ሰማንታ ሀይሉ/(Samantha Powers)
ዛሬስ ፈጣሪዋ ምን ብልዋት ይሆናል
ሂብራይስት ባንሆንም መልክት ይገባናል
የሰማይ የምድር ሀይል ተከናንባ በስም
ምን ልታደርግ መጣች ለቁጣ ለስላም?
ዕውቀት አካብታለች ድንክዬም አይደለች
ልምድም አላት አሉ ሰውን የማትሰለች
በደላላ ቛንቛ ወይንስ በሆዳችን
ሚሊዮን ድርሶናል ማባበያም ቢሆን
አስቲ እጠብቃለሁ ነቃ ብዬ ዛሬ
ነፋሱ ከሁዋላ ይምጣላት ላገሬ።
ሀገር ወዳድ ሎስ አንጀለስ
ዛሬስ ፈጣሪዋ ምን ብልዋት ይሆናል
ሂብራይስት ባንሆንም መልክት ይገባናል
የሰማይ የምድር ሀይል ተከናንባ በስም
ምን ልታደርግ መጣች ለቁጣ ለስላም?
ዕውቀት አካብታለች ድንክዬም አይደለች
ልምድም አላት አሉ ሰውን የማትሰለች
በደላላ ቛንቛ ወይንስ በሆዳችን
ሚሊዮን ድርሶናል ማባበያም ቢሆን
አስቲ እጠብቃለሁ ነቃ ብዬ ዛሬ
ነፋሱ ከሁዋላ ይምጣላት ላገሬ።
July 29, 2021 ሐምሌ 22 2013
የሕወሐት/የትግራይ ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ ሰላም
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ጦርንት በትኩስ አቁም ትእዛዝ (ዩኒላቴራል ሲዝ ፋየር) በማስቆም ከትግራይ ክልል የኢትዮጵያን ሠራዊት ካስወጣ አንድ ወር ሆኖታል። ሕወሐት ግን ጦርነቱን ኢትዮጵያ ላይ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ወጥቶ ደጀን ይሆኑኛል በሚላቸው አጎራባች ክልሎች ጠምዶ የመከላከል ጦርንት እያካሄደ ይገኛል።
ሕወሐት በምሥራቅ (አፋር ክልል) በደቡብና ምዕራብ (አማራ ክልል) የሰው ማዕበል መፍጠር በሚል የውግያ ስልት በሕፃናት የታጀበ የትንኮሳ ጦርነቶች በተደጋጋሚ ታካሂዳለች። ሕወሐት የትግራይን ህዝብ እያስጨረች ነው። በእርዳታ የተገኙ እህል የጫኑትን መኪናዎች ለትግራይ ህዝብ እንዳይደርስ የማድረግ አንቅፋቶች ትፈጥራለች።(መኪናዎችን ማቃጠል፤ መንገዶችን መዝጋት፤ ተኩስ መክፈት ወዘተ… ) የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይን ህዝብ ኣውቆ በረሀብ እንዲያልቅ ይፈልጋል ብላ ሕወሐት በዓለም አቀፍ ፊት ለመክሰስ/እዬዬ ለማለት እንዲመቻት ነው። በየቀኑ የምንስማው የድል አሸናፊነት ዜና/ፕሮፓጋንዳ ግን በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሐትም አየተካሄደ ነው።
የምእራብ ሀያላን የትግራይ ጉዳይ ያሳስበናል በማለት ለሕወሐት እርዳታችውን በተለየ አደረጃጀትና ቅንብር ቀጥለዋል (የሀሳብ፤የቆሳቁስ ፤የስለላ፤በአለም መገናኛ ብዙሃን ፕሮፓጋንዳ መርጨት ወዘተ… ) መከራችንን ትኩረት ሰጥተው ያጦዙታል ለማለት ነው።
እንዲህ ዐይነት መከራችን የሚረግበውና ወደ ሰላም መሄድ የምንጀምረው ሕወሐት ተኩስ ስታቆምና ወደ ውይይት ለማድረግ ስትወስን ብቻ ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ (የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ) ከሁሉ በፊት የሚያስፈልገዉ ሰላም ነው። ሰላምን ለማምጣት ተኩስ ማቆሙ የግድ ነው።
እንደሚታወቀው ሕወሐት በስሜን እዝ ላይ ባካሄደችው የሀገር ክህደት ምክንያት፤ የኢትዮጵያ መንግስት የዚህን ክህደት በአቀነባባሪነት የተሳተፉትን ለመያዝ የህግ ማስከበር ዘመቻ አካሂዷል ።በዚህ የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ብዙ የሰው ሞት፡የመብት ጥሰቶች ፤የሴቶች መደፈር ፤የዘር ማጥፋት ድርጊቶች፤ ብዙ የንብረት መጥፋትንና መውደም በሰፊው የተነገረ ቢሆምን፤ ምን ያህሉ እውነት ምን ያሉ የፕሮፖጋንዳ ውጤት እንደሆነ ለማወቅ በጣም ያስቸግራል/ይከብዳል።
ይኼ ሁሉ ሊጣራ የሚችለው በገልልተኛ ተቋማት ብቻ ነው። ሰላም በሌለበት ግን ይሄም ሊካሄድ አይችልም።
በድርድር ወይም በውይይት ከተቀመጠ፡ሕወሐት ብዙ የድርድር ወይም የውይይት ጥያቄዎችን ታቀርባለች ብለን እንገምታለን።
የኢትዮጵያ መንግስት መከተል አለበት ብለን የምናምናቸውን ሶስት (3) መሰረታዊ ሃሳቦችን እንደሚከተለው እናቀርባለን፤
የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያውያ ሉአላዊነት ላይ መደራደር ወይም መወያየት የለበትም፤ ለአጀንዳም መቅረብ የለበትም።
በህግ ማስከበር ዘመቻ የሚፈሉጉ ከሃዲዎችና ከዚያ በፊት ማዘዣ የወጣባቸው ወንጀለኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ መስጠት አለባቸው።
የተቀረው ለኣጀንዳ የሚቅርቡ ሃሳቦች በሙሉ በድርድር መሆን አለበት ።
ኢትዮጵያ በሰላምና በክብር ለዘላለም ትኑር!!
የፍትህ መጽሔትን አትርሱኝ
ላለፉት ብዙ ወራት የአሜሪካ መንግሥት ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ቢሊንከን ጋር የተቀነባበረና አብዛኛውን ጊዜ ባልተረጋገጡ መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ የኢትዮጵያን ስም የሚያጠፉ ብዙ ዘመቻዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ አካሂደዋል።
ይኼውም ኢትዮጵያውያ በትግራይ ክልል የሚታደርገውን የሕግ ማስከበር አንድም ቀን አንቶኒ ቢልከንና የአውሮፓ አጫፋሪዎቻቸው (እንደ አየርላንድ፣ ፊንላንድና እንግሊዝ ) እንዲሁም ሌሎች ፤የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለው ወንጀለኞችን የመያዝና የሕግ ማስከበሪያ ዘመቻ መሆኑን አይናገሩም። ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል አይናገሩም።
ግን ወንጀሉን የፈፀሙት ህወሓቶች በራሳቸው አንደበት በራሳቸው መገናኛ በትግራይ ቲቪ እንዲሁም በአመሪካ ውስጥ ባለው ትግራይ ሚዲያ ሐውስ ለዓለም ሕዝብ እንዴት አድርገው በቅፅበት እስራኤሎች የግብፅን ጦር እንደ ደመሰሱት የኢትዮጵያን የሴመን እዝ እንደ ደመሰሱ በፉከራ ይናገራሉ።
እንግዲህ አንድ ተረት ያለ ይመስለኛል። ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል የሚለው ነው። አሜሪካኖች ለምንድነው የጅራፉን ጩሄት ያመኑት? ይኼ ሴራ አስቅድሞ የተጠነሰሰ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አለን።
አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ባለ በሌለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ትከሳለች። መረጃዎቹ በነአሉላ ሰለሞን የሚቀነባበር ከአሉባልታ ደረጃ የሚቆጠር ሲሆን፤አሉላ በቀጠራቸው ሎቢሰቶች የሚቀረቡ ናቸው።
አመሪካ የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአማራ ኃይልም ከትግራይ እዲወጣ ይነዘንዛሉ። ቁጣ የተሞላበት ትዛዙ ማለቂያ የለውም። አንቶኒ ቢሊንከን ሲደመጡ ኢትዮጵያን የአሜሪካን ግዛት ወይም ቅኝ ግዛት በሚያስመስል አይነት ነው የሚናገሩት። ኢትዮጵያውያ ሉዑላዊ አገር መሆኗን ረስተው አይደለም። እንዲህ በማለት የመልክቱ ግፊት ሲፈለቀቅ ሲወጣ/ሲጋለጥ ተደራደሩ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥትን ለመለወጥ ዝግጅት ላይ እንዳሉ የሚያሳዩ ሁኔታዎች አንዳሉም እንገምታለን። የግለሰብ ስሞች በአደባባይ ይጠራሉ። ሩጫም የተያዘ ይመስላል …ውይይት አድርጉ ምርጫችሁ ይኼ ብቻ ነው ይላሉ።
ፍትህ መጽሔት አሁን በቅርብ ጊዜ ማለትም በ17/07/2021 በርዕሰ አንቀፅ አውጥታ ያቀረበችው “ለትግራይ ብቸኛው አማራጭ ድርድርና ውይይት ብቻ ነው” የሚል ርእስ ሲሆን፤ ይህ ሀሳብ እዚህ በአመሪካን የሚመለመሉትን የኢትዮጵያ ጫላቢዎች( ማለት…በአሜሪካኖች የተመረጡ ወይንም የሚመረጡ አገልጋዮች …”አሜሪካ እኔ እሻልሻለሁ” እያሉ የሚጮሁና የሚወዳዳደሩትንም ይጨምራል) ። ፍትህ መፅፄት ይንን ሀሳብ ትደግፋለች (ኢንዶርስ) ታደርጋለች።
ዋና ዋና የድርድርና የውይይት ሃሳቦች ብላ ደግሞ መጽሔቷ የጠቀሰችው ሁለት ናቸው። የማንነት ጥያቄና የወሰን አከላለል የሚል ዓላማ ያለው ይመስላል። የመጽሄቷ አቋምና/ጩኸት እስረኞች ይፈቱ፣ ውጭ ያሉ ግለሰቦች ይመለሱ አያለች አሜሪካኖችን ቴሌግራፍ ታደርጋለች ። ከአሜሪካኖች ለመናበብ ትሞክራለች ለማለት ነው። እንዲያውም ማመልከቻ ማስገባት ሳይሆንም አይቀርም።
ኢትዮጵያውያ ውስጥ ሁለት ወይም ሦስት አሥርተ ዓመታት የኖረ ሰው የህወሓትን ማንነትና ጠባይን ማወቅና መገመት ይችላል ። ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ያቀዱትን ሥራ ላይ እያዋሉ ይገኛሉ።
ይኸውም ፤
◦ ትልቋን ትግራይ መመሥረት። ይህንንም ለማድረግ በ1976 የነበረችውን ትግራይን ግዛት ማስፋፋት (የአሁኑን የወሰን አከላለል ችግርም የመጣው ከዚሁ ከትግራይ ግዛት መስፋፋት ነው)።
◦ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተነደፈው እዚያው ደደቢት በረሃ ነው ብለን ስለምንገምት። (ፍትህ መጽሔት የህወሓትን የ1976 ማኒፌስቶ የማታውቅ ይመስላል )።
◦ ያ ሁሉ የሽግግር መንግሥት ጉባኤ፣ ያ ሁሉ የሕግ ማርቀቅ ለእይታ የተካሄዱ ናቸው ብለን ስለምናምን።
◦ አቶ ስዬ ለአንዱ ኮንፈረንስ ተሳታፊ ጥያቄ ሲመልሱ “እናንተን እኮ ያመጣናችሁ እንድትታዩ እንጂ ሃሳብ እንድትሰጡ አልነበረም” ብሎ ስለነበር።
ተቦክቶ ተጋግሮ የመጣ ነበር ለማለት ነው። አንቀጽ 39ም በዚህ ሁኔታ ነው የጸደቀው። ከዚያ በኋላ ነው ኢትዮጵያውያን የመበተን ሥራ የተቀጣጠለው። አቶ ስዬ ዛሬም ተመልሰው ኢትዮጵያን ለመበታተን እየሠሩ ነው።
ፍትህ ግን ስለመገንጠል አሁን እያነሱ ነው ትላለች። የሕወሓት ኑሮ ምን ሆነና? ሕወሓት በሕይወቱ/በታሪኩ ውስጥ የተደራደረበት ጊዜ የለም። ተቃዋሚዎችን ከመደምሰስ ውጭ። በአንቀጽ 39 ሳቢያ ሥልጣን ላይ መመለስ ነው የሚፈልጉት።
ፍትህ መፅሄት በጣም ተሳስታለች። ከአሜሪካና ከሕወሃት ጋር መተባበር የለባትም። የጠ/ሚ አብይን መንግሥት ወይም ዶ/ር አብይን የሚጠሉ በአንድ ጎራ እየተሰባሰቡ ነው። የፍትህ አቅዋምን በቃላት አጣፍጦ መሸፋፈን ምንም ዋጋ የለውም ብለን እናሳስባለን።
July 24,2021
Don’t Bet on US, EU Predictions on PM Abiy’s Government
The “magic dragons” are puffing smoke again. The first puff was “no elections in Ethiopia’ until a consultative meeting with “stakeholders”, “opposition figures” and their favorite “bandits”, but the election took place peacefully and ended peacefully.
The second puff was mobilizing the world to block the second filling of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). At the United Nations Security Council, the non Western world voted against or abstained and did not buy into the West’s BS. But that is history now because the second GERD filling is completed.The dragons third puff was constant bitching for access in Tigray and they got it, but the bitching continues louder with all its hues and permutations.
And the puff now is “ a coup imminent ?” We have better odds with Ethiopian local wizards and witches who have better predictions than these dragons.
As Ethiopia walks, all be it a step at a time towards democracy, the behemoth modern day Goliath that is US roams the world with the most destructive power and darwinian mode of existence (eat or be eaten). It has also the prowess of the night king Dracula. It won’t hesitate to use its fangs (weapons) on anyone … just ask our neighbors in the region.
Poor countries are blown away directly and indirectly under one pretext or another and to the “victor goes the loot”, as one American general said after the overthrow of Saddam Hussein’s government and the looting of Iraq’s oil followed.
Prime Minister Abiy Ahmed’s democracy reforms and the recent elections is starting to out shine that of the US. PM Abiy is a Nobel Peace Prize recipient for reversing the longtime state of “no war no peace” and ended the border conflict with Eritrea.
One morning in1962 as a young boy in Addis, I was walking to a church nearby to serve an early morning mass and from an open window across the street a beautiful lady hollered at me profanities for no reason. I couldn’t keep my eyes off of her stunning face, but the words coming out of her mouth blistered my little heart. She was a prostitute.
Today’s profanities that come out from unsavory foreign “diplomats” in high places can bleed not only the heart of the meek but shake up the faith of an enduring friendship of a nation.
The “he said she said” acrimonies to create further chaos and divisions among Ethiopians from external actors and “diplomats” in the country truly requires attention. The government of PM Abiy has through his minister, Mr. Redwan warned “diplomats” to behave or face steel toed booting out of the country.
The TPLF goons continue their probing attacks in small villages and towns using children soldiers. TPLF hungry kids are forced to loot whatever they get their hands on to survive. It has turned them into roving bandits. They shoot on aid trucks entering Mekele and some among them are selected by the TPLF cadres to give a small spiel to foreign agents so that they write or make noise globally on their behalf.
Encircling of Tigray by Ethiopian regional armies and the ENDF has put the TPLF in check for now and according to the Generals Jula and Bacha, they are biding their time and waiting for their marching orders from the political leadership of PM Abiy, who is determined to fight on his own terms.
መልዕክት… ውጪና አገርቤት ላሉ ኢትዮጵያኖች በሙሉ።
ዶክተር አቢይ ወደ ሥልጣን እንደመጡ አንዱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡት ቃል መገናኛ ብዙሃንን (ሚዲያዎችን) ነፃ ማድረግ ነበር። እስካሁን ድረስ ዶክተር አቢይ ይኼንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡትን ቃል አክብረዋል። ማንበቡን ስትቀጥሉ ይኼ ሀሳብ ግልፅ ይሆናል።
እስካሁን እደሚታየው የግል መገናኛ ብዙሃን ትንተና ከአገር ገንቢ ሀሳብ አንስቶ እስከ አገር አፍራሽ የሆኑ ሀሳቦችን ሲያቀርቡ ይደመጣሉ። አንዳንዶቹ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ብሔር ተኮር ናቸው።በተለይ የክልሎቹ ። ሌሎችም የግል የሆኑ ብሔር ተኮር የሆኑ አሉ/ነበሩ።
ኢትዮጵያውያ ውስጥ ዋልታ ረገጥ ሀሳቦች ላለፉት ሦስት ዓመታት እንደልብ ሲቀርቡ ሲለፈፉ ሲተቹ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹ አስተያየቶች ለሰው ልጆች ሕይወት መጥፋት፡ ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል። አንዳንዶቹ ሃሳቦች የኢትዮጵያኖችን ህልውና በማደንዘዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ ለመቀልበስ ሌት ተቀን ሲታታሩ ይታያሉ።
ሁለቱን ማለት ኢትዮ 360ና የትግራይ ቴሌቪዥን / የትግራይ ሚዲያ ሐውስን እንጥቅስ። የሁለቱ ዐላማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሳካ ማድረግ ነው። አመጣጣቸው ከሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች ነው። የትግራይ ቴሌቪዥን / ትግራይ ሚዲያ ህዋስን ማስረዳት አያስፈልግም። ምክንያቶቹ ግልፅ ስለመሰለን። የኢትዮ 360ን ለማስረዳት የሚከተሉትን እንይ።
ለአለፉት አመታት ከኢሳት ተገጥለው እራሳቸውን ኢትዮ 360 ብለው መጠራት ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ(አራት አቅራቢዎች) ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው የኢትዮጵያውያን ዜጎችን እርስ በርሳቸው እንዲጠራጠሩ ሰፋ ያለ ሥራ ሰርተዋል። ኦሮሞው አማራውን፡ አማራው ኦሮሞን እንዳያምን የጥላቻ መርዝ ረጭተዋል። በትግራይ ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን / የትግራይ ሚዲያ ሐውስ ዶክተር አብይን አሃዳዊ ጨፍላቂ እይያሉ ሲግልፁ፡ የ360ዋ እንስት ደግሞ የኦሮሙማ የበላይነት አደጋ ኢትዮጵያውያ ላ መጥቷል እያለች ሁለቱም አንድላይ በመሆነ በየአቅጣጫው የሚስብኩት ሁለት ወይም ሦስት ግቦችን መቶላቸዋል።
በግንባር ቀደምትነት እነዚህ ግለሰቦች ሁሉንም የለውጡ ሪፎርሞችን በኦሮሙማ መነፅር በማየት ሥራቸው መቃወም ወይም ማቀርሸት ነው።የሚሊታሪ ሪፎርም፣ የፍርድ ቤቶች፣የምርጫ ሕግና የምርጫ ቦርድ መዋቅር… ወዘተ የመሣሠሉትን ለውጦች ባልተሟሉ መረጃዎች ፤ አንዳንዴ ደግሞ ከኪሳቸው ባወጡት መረጃ የሚመስል ግን ፍብረካና/ልብ ወለዶችን በመጠቀም ለውጦቹን በሙሉ የኦሮሙማ ጥላሸት በመቀባት ነው።
ሌላው ድርጊታቸው ደግሞ ተቃዋሚ ነን በሚል ሰበብ የዶክተር አቢይን መንግሥት የሚቃወሙትንና ኢትዮጵያውያን ለማፍረስ በሚጥሩ የሚታወቁ ግለሰቦችን በመጋበዝ “ኦሮሞ መጣብህ ” የሚለውን ሆይሆይታ ማስተጋባት ነው።
ይኼ ሁሉ የሚደረገው ደግሞ ዋሽንግተን ዲሲ እስቱዲዮ ውጥ ቁጭ ብለው ነው። ቀንደኛ/አውራ የሚመስልው ሰውዬ ደግሞ መጽሔት ከጀርባው በመደርደር አዋቂነቱን ለማሳየት በሚመስል ይሄ ማትስ 101 ነው፡ ይሄ ኢኮኖሚክስ 101 ነው ይሄ ሳይኮሎጂ 101 እያለ በዚያን ቀን በሚያወራው አርእስት የዶክተር አብይን አለማወቅ ለማሳየት ሲሞክር፡ ከዚህ በኋላ ሁሉም ባንድ ላይ ዶክተር አቢይን እንደተራ ሰው ክቡሩን በማሳነስ፤እንደተራ መንገደኛ መምራት የማይችል ፡የዞረበት፤ አገሪቱ መሪ የሌላት እያሉ ተራ በተራ የአስተሳሰባችውን ክብደት በሚመዝን/በሚያጋልጥ ቃላቶችን ሲቀባበሉ ይታያሉ። ልጅቷም ዶክተር አብይን ለማጥቃት በሚል ይመስላል የሰውን ህሊና በሚያስክፉ ቃላት ጥያቄዎችን ታቀርባልች።ይሄ በኢትዮ 360 የሚታይ የየቀኑ ከኣማኑኤል የሚላክ መልክት ነው።
ይኼ ሁሉ የሚደረገው ለአማራው ሕዝብ ጥብቅና መቆም በሚል ነው። አውራው በአለፉት 15ና 20 ዓመታት የአማራን ሕዝብ ያስጠቃ ፡ንሰሃ ምን መሆኑን ያልተረዳ ስለሆነ ሕብረተሰባችን አፍ ከመያዝ ምን ይበል? አማራውን ብቸኛ የማድረግ አባዜም ከመቀሌም የሚሰማ ጩሄት መሆኑንም ይገነዘብ ይሆን?
አሳዛኙ ግን ኢትዮጵያውያ ውስጥ ብዙ ወጣቶች በዚህ በሚዲያ ሥራ የተሰማሩ ተስፋ የሚጣልባቸውና ችሎታቸው በደንብ የሚታይ ሆኖ ሳለ አንዳንዶቹ ግን በኢትዮ 360 ቫይረስ የተበከሉ ይመስላል። ለምሳሌ አውድማ ፕሮግራም ጥሩ ሆኖ ሳለ ወጣቶቹ የግድ ጥሩውን ነገር ለማፍረስ የግድ ድንጋይ መፈንቀል ያለባቸው ይመስላቸዋል። በነገራችን ላይ አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ ሀሳብ ለመስጠት ደግሞ ሦስት ሰዎች አያስፈልጉም።
በሦስተኛ ደረጃ አመሪካ ውስጥ እንዲህ ዓይነት እንደ ኢትዮ 360 ሚዲያ ያሉት የገቢ ምንጭ መሆናቸውን አንዘንጋ። የግለሰቦችን ስሜት ቀስቅሶ ፡አስለቅሶ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ባልተረጋገጠ መrvጃ “አሁን የደረሰን” በሚል አስደንጋጭ መልክት ገንዘብ መሰብሰብ ነው።
እንደኛው እኛ በበጎ ፈቃዳችን የምንገብረው ሲሆን ፡ “ያቺን ደወል ስንጫን” ዩቱብም ዶላር ይከፈላቸዋል። የሚጮሁት ታዲያ ለምን መሰላችሁ? አረንጓዴው ዶላር እየታያቸው ነው። በልባቸው እየሳቁ ዶላርዋን ይዘው ወደ ባንክ ቤት ይሮጣሉ። አንዳንድ ቀን ዛሬ ብዙ ተመልካች አለን ብለው የሚደሰቱት ለምን እንደሆነ ይገባችኋል።
የነዚህ ታሪክ ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም። እስክንድርን/ባልደራሰን አብንንም ሲጠቀሙ ይታያሉ። እይታውና አካሄዱ ጀርባዬን እከከኝ ጀርባህን ልከክልህ ይመስላል።
አብዛኛውን ጊዜ ሲመፃደቁ ይሰማሉ። “የዛሬ ሁለት ዓመት” “የዛሬ ዓመት” እያሉ ጊዜ በመቁጠር “ለአብይ ነግረነው ነበር” ሲሉ ይሰማሉ። የዶክተር አቢይን ፖሊሲ አንድም ቀን በእውነት ሲናገሩ አይሰሙም።
አንዱማ ለዶክተር አቢይ የለውጥ ሮድ ማፕ ሰጠሁ ያለው እስር ቤት ነው። እነዚህ ደግሞ እሱን መተካታቸው ይሆን? አስር ቤት ያለው ኦሮሞን አነሳስቶ አማራ ላይ እዲዘምት ነበር። እነዚህኞቹ ከመቕለ ጋር በመናበብ ላለፉት ዘመናት ያካሄዱትን እንደገና ለማካሄድ ማለት አማራው ከኦሮሞ እንዲጋጭ ሙከራ እያደረጉ ነው። አንሞኝም … ነቅተናል እንበላቸው።
በተለይ ምዕራባዊያን በአሜሪካ መሪነት አገራችን ላይ እየተካሄደ ያለውን “የወያኔን ግርግር” በመጠቀም የጎነጎኑትን ሴራ ለማከናወን የዘመኑ “ጫላቢዎች” ማለትም በሻለቃው በዳግመ ልደትና ባንድራ አጃቢን በማሰለፍ ኢትዮጵያ ለመግባት የተዘጋጁ ይመሰላሉ።
እስከአሁን ያየነው የኢትዮ 360 ባሕሪይ ዐላማውና ጠባዩ የአቢይን መንግሥት መገልበጥ ወይም ማስገልበጥ ሲሆን ፡ እግረመንገዳቸውንም በአረንጓዴ ዶላር መክበር ነው። ውጭ ላለነው የሚታየን ግምት ስለሆነ አገር ውስጥ ካላችሁትም አንጋራው ብለን ነው።
ቸር ይግጠመን!