የፍትህ መጽሔትን አትርሱኝ

ላለፉት ብዙ ወራት የአሜሪካ መንግሥት ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ቢሊንከን ጋር የተቀነባበረና አብዛኛውን ጊዜ ባልተረጋገጡ መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ የኢትዮጵያን ስም የሚያጠፉ ብዙ ዘመቻዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ አካሂደዋል።

ይኼውም ኢትዮጵያውያ በትግራይ ክልል የሚታደርገውን የሕግ ማስከበር  አንድም ቀን አንቶኒ ቢልከንና የአውሮፓ አጫፋሪዎቻቸው (እንደ አየርላንድ፣ ፊንላንድና እንግሊዝ ) እንዲሁም ሌሎች ፤የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለው ወንጀለኞችን የመያዝና የሕግ ማስከበሪያ ዘመቻ  መሆኑን አይናገሩም። ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል አይናገሩም።

ግን ወንጀሉን የፈፀሙት ህወሓቶች በራሳቸው አንደበት በራሳቸው መገናኛ በትግራይ ቲቪ እንዲሁም በአመሪካ ውስጥ ባለው ትግራይ ሚዲያ ሐውስ ለዓለም ሕዝብ እንዴት አድርገው በቅፅበት እስራኤሎች የግብፅን ጦር እንደ ደመሰሱት የኢትዮጵያን የሴመን እዝ እንደ ደመሰሱ በፉከራ ይናገራሉ።

እንግዲህ አንድ ተረት ያለ ይመስለኛል። ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል የሚለው ነው። አሜሪካኖች ለምንድነው የጅራፉን ጩሄት ያመኑት? ይኼ ሴራ አስቅድሞ የተጠነሰሰ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አለን። 

አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ባለ በሌለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ትከሳለች። መረጃዎቹ በነአሉላ ሰለሞን የሚቀነባበር ከአሉባልታ ደረጃ የሚቆጠር ሲሆን፤አሉላ በቀጠራቸው ሎቢሰቶች የሚቀረቡ ናቸው።

አመሪካ የኢትዮጵያ የጦር ኃይልና የአማራ ኃይልም ከትግራይ እዲወጣ ይነዘንዛሉ። ቁጣ የተሞላበት ትዛዙ ማለቂያ የለውም። አንቶኒ ቢሊንከን ሲደመጡ ኢትዮጵያን የአሜሪካን ግዛት ወይም ቅኝ ግዛት በሚያስመስል አይነት ነው የሚናገሩት። ኢትዮጵያውያ ሉዑላዊ አገር መሆኗን ረስተው አይደለም። እንዲህ በማለት የመልክቱ ግፊት ሲፈለቀቅ ሲወጣ/ሲጋለጥ ተደራደሩ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥትን ለመለወጥ ዝግጅት ላይ እንዳሉ የሚያሳዩ ሁኔታዎች አንዳሉም እንገምታለን። የግለሰብ ስሞች በአደባባይ ይጠራሉ። ሩጫም የተያዘ ይመስላል ውይይት አድርጉ ምርጫችሁ ይኼ ብቻ ነው ይላሉ።

ፍትህ መጽሔት አሁን በቅርብ ጊዜ ማለትም በ17/07/2021 በርዕሰ አንቀፅ አውጥታ ያቀረበችው ለትግራይ ብቸኛው አማራጭ ድርድርና ውይይት ብቻ ነውየሚል ርእስ ሲሆን፤ ይህ ሀሳብ እዚህ በአመሪካን የሚመለመሉትን የኢትዮጵያ ጫላቢዎች( ማለትበአሜሪካኖች የተመረጡ ወይንም የሚመረጡ አገልጋዮች …”አሜሪካ እኔ እሻልሻለሁእያሉ የሚጮሁና የሚወዳዳደሩትንም ይጨምራል) ። ፍትህ መፅፄት ይንን ሀሳብ ትደግፋለች (ኢንዶርስ) ታደርጋለች።

ዋና ዋና የድርድርና የውይይት ሃሳቦች ብላ ደግሞ መጽሔቷ የጠቀሰችው ሁለት ናቸው። የማንነት ጥያቄና የወሰን አከላለል የሚል ዓላማ ያለው ይመስላል። የመጽሄቷ አቋምና/ጩኸት እስረኞች ይፈቱ፣ ውጭ ያሉ ግለሰቦች ይመለሱ አያለች አሜሪካኖችን ቴሌግራፍ ታደርጋለች ። ከአሜሪካኖች ለመናበብ ትሞክራለች ለማለት ነው። እንዲያውም ማመልከቻ ማስገባት ሳይሆንም አይቀርም።

ኢትዮጵያውያ ውስጥ ሁለት ወይም ሦስት አሥርተ ዓመታት የኖረ ሰው የህወሓትን ማንነትና ጠባይን ማወቅና መገመት ይችላል ። ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ያቀዱትን ሥራ ላይ እያዋሉ ይገኛሉ።

ይኸውም ፤

ትልቋን ትግራይ መመሥረት። ይህንንም ለማድረግ በ1976 የነበረችውን ትግራይን ግዛት ማስፋፋት (የአሁኑን የወሰን አከላለል ችግርም የመጣው ከዚሁ ከትግራይ ግዛት መስፋፋት ነው)

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተነደፈው እዚያው ደደቢት በረሃ ነው ብለን ስለምንገምት። (ፍትህ መጽሔት የህወሓትን የ1976 ማኒፌስቶ የማታውቅ ይመስላል )

ያ ሁሉ የሽግግር መንግሥት ጉባኤ፣ ያ ሁሉ የሕግ ማርቀቅ ለእይታ የተካሄዱ ናቸው ብለን ስለምናምን።

አቶ ስዬ ለአንዱ ኮንፈረንስ ተሳታፊ ጥያቄ ሲመልሱ እናንተን እኮ ያመጣናችሁ እንድትታዩ እንጂ ሃሳብ እንድትሰጡ አልነበረምብሎ ስለነበር።

ተቦክቶ ተጋግሮ የመጣ ነበር ለማለት ነው። አንቀጽ 39ም በዚህ ሁኔታ ነው የጸደቀው። ከዚያ በኋላ ነው ኢትዮጵያውያን የመበተን ሥራ የተቀጣጠለው። አቶ ስዬ ዛሬም ተመልሰው ኢትዮጵያን ለመበታተን እየሠሩ ነው።

ፍትህ ግን ስለመገንጠል አሁን እያነሱ ነው ትላለች። የሕወሓት ኑሮ ምን ሆነና? ሕወሓት በሕይወቱ/በታሪኩ ውስጥ የተደራደረበት ጊዜ የለም። ተቃዋሚዎችን ከመደምሰስ ውጭ። በአንቀጽ 39 ሳቢያ ሥልጣን ላይ መመለስ ነው የሚፈልጉት።

ፍትህ መፅሄት በጣም ተሳስታለች። ከአሜሪካና ከሕወሃት ጋር መተባበር የለባትም። የጠ/ሚ አብይን መንግሥት ወይም ዶ/ር አብይን የሚጠሉ በአንድ ጎራ እየተሰባሰቡ ነው። የፍትህ አቅዋምን በቃላት አጣፍጦ መሸፋፈን ምንም ዋጋ የለውም ብለን እናሳስባለን።