July 29, 2021                   ሐምሌ 22  2013 

የሕወሐት/የትግራይ ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ ሰላም    

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ጦርንት በትኩስ አቁም ትእዛዝ (ዩኒላቴራል ሲዝ ፋየር) በማስቆም ከትግራይ ክልል የኢትዮጵያን ሠራዊት ካስወጣ አንድ ወር ሆኖታል። ሕወሐት ግን ጦርነቱን ኢትዮጵያ ላይ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ወጥቶ ደጀን ይሆኑኛል በሚላቸው አጎራባች ክልሎች ጠምዶ የመከላከል ጦርንት እያካሄደ ይገኛል።

ሕወሐት በምሥራቅ (አፋር ክልል) በደቡብና ምዕራብ (አማራ ክልል) የሰው ማዕበል መፍጠር በሚል የውግያ ስልት በሕፃናት የታጀበ የትንኮሳ ጦርነቶች በተደጋጋሚ ታካሂዳለች። ሕወሐት የትግራይን ህዝብ እያስጨረች ነው።   በእርዳታ የተገኙ እህል የጫኑትን መኪናዎች ለትግራይ ህዝብ እንዳይደርስ የማድረግ አንቅፋቶች ትፈጥራለች።(መኪናዎችን ማቃጠል፤ መንገዶችን መዝጋት፤ ተኩስ መክፈት ወዘተ… ) የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይን ህዝብ ኣውቆ በረሀብ እንዲያልቅ ይፈልጋል ብላ ሕወሐት በዓለም አቀፍ ፊት ለመክሰስ/እዬዬ ለማለት እንዲመቻት ነው። በየቀኑ የምንስማው የድል አሸናፊነት ዜና/ፕሮፓጋንዳ ግን በኢትዮጵያ መንግስትና በሕወሐትም አየተካሄደ ነው።

የምእራብ ሀያላን የትግራይ ጉዳይ ያሳስበናል በማለት ለሕወሐት እርዳታችውን በተለየ አደረጃጀትና ቅንብር ቀጥለዋል (የሀሳብ፤የቆሳቁስ ፤የስለላ፤በአለም መገናኛ ብዙሃን ፕሮፓጋንዳ መርጨት ወዘተ… ) መከራችንን ትኩረት ሰጥተው ያጦዙታል ለማለት ነው።

እንዲህ ዐይነት መከራችን የሚረግበውና ወደ ሰላም መሄድ የምንጀምረው ሕወሐት ተኩስ ስታቆምና ወደ ውይይት ለማድረግ ስትወስን ብቻ ነው።  ለኢትዮጵያ ሕዝብ (የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ) ከሁሉ በፊት የሚያስፈልገዉ ሰላም ነው። ሰላምን ለማምጣት ተኩስ ማቆሙ የግድ ነው።

እንደሚታወቀው ሕወሐት በስሜን እዝ ላይ ባካሄደችው የሀገር ክህደት ምክንያት፤ የኢትዮጵያ መንግስት የዚህን ክህደት በአቀነባባሪነት የተሳተፉትን ለመያዝ የህግ ማስከበር ዘመቻ አካሂዷል ።በዚህ የህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ብዙ የሰው ሞት፡የመብት ጥሰቶች ፤የሴቶች መደፈር ፤የዘር ማጥፋት ድርጊቶች፤ ብዙ የንብረት መጥፋትንና መውደም በሰፊው የተነገረ ቢሆምን፤ ምን ያህሉ እውነት ምን ያሉ የፕሮፖጋንዳ ውጤት እንደሆነ ለማወቅ በጣም ያስቸግራል/ይከብዳል።

ይኼ ሁሉ ሊጣራ የሚችለው በገልልተኛ ተቋማት ብቻ ነው። ሰላም በሌለበት ግን ይሄም ሊካሄድ አይችልም።

በድርድር ወይም በውይይት ከተቀመጠ፡ሕወሐት ብዙ የድርድር ወይም የውይይት ጥያቄዎችን ታቀርባለች ብለን እንገምታለን።

የኢትዮጵያ መንግስት መከተል አለበት ብለን የምናምናቸውን ሶስት (3) መሰረታዊ ሃሳቦችን እንደሚከተለው እናቀርባለን፤

    1. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያውያ ሉአላዊነት ላይ መደራደር ወይም መወያየት የለበትም፤ ለአጀንዳም መቅረብ የለበትም።

    2. በህግ ማስከበር ዘመቻ የሚፈሉጉ ከሃዲዎችና ከዚያ በፊት ማዘዣ የወጣባቸው ወንጀለኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ መስጠት አለባቸው።

    3. የተቀረው ለኣጀንዳ የሚቅርቡ ሃሳቦች በሙሉ በድርድር መሆን አለበት ።

ኢትዮጵያ በሰላምና በክብር ለዘላለም ትኑር!!