ሰማንታ ሀይሉ/(Samantha Powers)

ዛሬስ ፈጣሪዋ ምን ብልዋት ይሆናል

ሂብራይስት ባንሆንም መልክት ይገባናል

የሰማይ የምድር ሀይል ተከናንባ በስም

ምን ልታደርግ መጣች ለቁጣ ለስላም?

ዕውቀት አካብታለች ድንክዬም አይደለች

ልምድም አላት አሉ ሰውን የማትሰለች

በደላላ ቛንቛ ወይንስ በሆዳችን 

ሚሊዮን ድርሶናል ማባበያም ቢሆን

አስቲ እጠብቃለሁ ነቃ ብዬ ዛሬ

ነፋሱ ከሁዋላ ይምጣላት ላገሬ።