ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና  "በግልፅ ቋንቋ" ክፍል ፩

ፕሮፌር መረራ ጉዲና አሁን ያሉት አሜሪካ ውስጥ ነው:: አሜሪካ አገር የሚቆዩት አንድ ወር ተኩል ነው:: በዚህ አንድ ወር ተኩል  ውስጥ 15የሜሪካ የታውቁ ከተሞችን ይጎበኛሉ:: እነዚህም ከተሞች በቅደም ተከል 1)ፊላደልፍያ፣ 2)ሳንፍራንስኮ፣ 3)ሳንዲያጎ፣4)ዳላስ፣5)ደንቬር፣6)ሲያትል፣ 7)ፖርትላንድ፣8)ላስቬጋስ፣ 9)አትላንታ፣ 10)ኮለንቦስ ኦሀዮ፣ 11)መኒሶታ፣ 12)ኒዮርክ፣ 13)ቦስተን፣ 14)ቺካኮና15)ዲሲ ናቸው::

ሃሳቤ ፕሮፌሰሩ የሚሄዱበትን ከተሞች ደጋፊዎቻቸው ሆነ  ተቋዋሚዎቻቸው በግልፅ  እንድያውቁ ብዬ ነው:: 

የዚህን ፅሑፍ ርእስ በዚህ መልክ ያስቀመጥኩበት ምክንያት ብዙ ጊዜ ፕሮፌሴር መረራ ጉዲና  ሲናገሩ በደንብ ካዳመጣችሁ  ደጋግመው ደጋግመው የሚሉት የቃል አጠቃቅም አለ:: በተለይ ከልባቸው መናገራችውን ለማሳመን ሲሞክሩ የሚሉት ቃል ነው:: ይኼም ቃል በግልፅ ቋንቋ” የሚል ነው:: ፕሮፌሰሩ ለምን እንደዚህ እንደሚሉ ያለኝን ግምትና አስተያየት እመለስበታለሁ:: 

በፕሮፌሰሩ  አቀራረብ አሜሪካን አገር ከሁለት ዓመት በኃላ ተመልሰው መምጣታቸው በአሜሪካ ውስጥ ካሉ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥና: የኦሮሞ ህዝብን ትግል በገንዘብ እንዴት ማገዝ እንደሚቻል ለመወያየት ነው::  በሌላ አነጋገር አመሪካን አገር የመጡት ገንዘብ  ለመለመን  ነው:: በግልፅ ቋንቋሲነገር ሀቁ  ይኼው ነው:: 

ሁለተኛው ደግሞ እግረመንገዳቸውን ደጋግመው እንደሚሉት የውጭ አገር ድርጅቶች ወይም ዜጎች ከኛ  ፓርቲ  (ኦፈኮ ማለት ነው) ፤ ጋር ይወያያሉ ሲሉ ተናግረዋል:: ፈረንጆችም  እግዚአብሔርም የሚረዳው እራሱን የሚረዳን ሰው ነውየሚሉትን ፈሊጥ የሚከተሉ ይመስላል :: ውጭ ካሉ ደጋፊዎች የገንዘብ ዕርዳታ ለመሰብሰብ ያላቸውን ፍላጎትና ዕቅድ በግልፅ ቋንቋአስቀምጠዋል። ሌላው የመጡት እስከአሁን  ድረስ ከነዚህ የውጪ አገር ተሰብሳቢዎች /ተወያዮች ጋር የደረሱበትን ስምምነት/ውሳኔ ስራ ላይ ለማዋል ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል:: ተጨማሪ ሃሳብ ላይም ለመወያየትም ሊሆን ይችላል:: እውነቱን እግዚአብሄርና አሳቸው ብቻ ነው የሚያውቁት:: 

አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያን ችግሮችን ለመፍታት በብዙ ጽሁፎቻቸው  ወይም ንግግሮቻቸው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚያዘወትሩት የውጭ ኃይሎችያስፈልጋሉ ነው:: እየተነጋገርን ነው:: የውጪዎችም ከኛ ሃሳብ ጋር  ይሰማማሉ:: ተወያዩ ተደራደሩ ይሉናል:: ስለዚህ እነሱን መስማት አለብን የሚሉ ሃሳቦችን ያራምዳሉ ይሰብካሉ:: እንደዚህ  ዐይነት አቋም መድረሳቸው የሚያሳዝን ነው:: 

ለመሆኑ ፕሮፌሰሩ ስለ ኢትዮዽያ ሀገርነት  ያላቸው አቋም ምንድነው?  ለኔ በግልፅ አነጋገርግልፅ አይደለም::  የሚከተለውን እንይ። 

አብዛኛውን ጊዜ ፕሮፌሰሩ እድሜያቸውን ያሳሉፍት በስልሳዎቹና በሰባዎቹ  የወጣቶች ትግል ዘመን የትግሉ ተሳትፊ ሆነው ነው:: የመኤሶን አባል ነብሩ ሲባል ስምቻለሁ::መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የመኤሶንን መፈክር  እራሳቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ:: የነቃ የተደራጀና የታጠቀ:: ወደዚህ መፈክር በሚቀጥለው ፪ኛ ክፍል ውስጥ እመለስበታለሁ። 

የመኤሶን አባል በመሆናቸዉ: በደርግ ዜመን ብዙ ዓመታት ታስረዋል:: የወንድማቸውም ሕይወት በዚህ በደርግ ጊዜ በትግል ማለፉ ይነገራል::ፕሮፌሰሩ በኢህአደግም ጊዜ ታስረዋል:: የተፈቱትም በለውጡ ሂደት ጊዜ ነው::  

2018  በምሕረት ሲፈቱ ከእስርቤት ከወጡ በሁውላ በተደረገላቸው አቀባበልና ባዩት የሕዝብ ማዕበል ስለራሳችውና ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው አስተሳሰብ በመሠረቱ የተቀየረ ይመስለኛል:: 

ይኼ አሁን  ያላቸው አቋም  ከእድሜ ጋር የመጣ ነዉ  ለማለት ይቻላል :: ወይም ደግሞ አቋማቸውን በወጣትነታቸው ጊዜ የኮት ኪሳቸው ውስጥ ደብቀው ይሆን የሚል  ጥያቄ ያስነሳል::  ያም ሆነ ይህ  በእኔ ግምት በስልሳዎቹና በሰባዎቹ  የነበራቸው  አቋም እውነተኛ  ነው ብዬ አምናለሁ ::  ምክንያቱም  ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ  ሥርዐትና መብት ሲሉ  ክነቤተሰባቸው  ዋጋ ከፍለዋል:: 

የስልሳዎችና ሳባዎቹ ትግልና መፈክሮች መሬት ለአራሹ ዲሞክራሲያዊ መብቶች  የብሕር እኩልነት ፍትሃዊነት የተስተካከለ የአስተዳደር ሥርዐት የሚሉ   ነበሩ::  ፕሮፌሰሩም በትግሉ ውስጥ የተሳተፉት በነዚህ መፈክሮች ስር ነው ብዬ አምናልሁ::ፕሮፌሰሩ በኢህእድግ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ፈደራላዊ መንግሥት የፓርላማ አባል  ወኪል ሆነው ለአመታት  አገልግለዋል:: በአገለገሉበት ጊዜም  በጣም ቀልደኛና አስቂኝ መሆናቸው ይነገራል ::

እሁን ወደ  ፕሮፌሰሩ ከእስርቤት መፈታት እንመለስ::  ፕሮፌሰሩ መስከረም 17  2018 በፈረንጆች አቆጣጠር  ባልሳሳት  ከእስርቤት የተፈቱበት ቀን ነው:: በሳቸዉ መፈታት  ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ  በአገር ውስጥም በውጭም  የሚኖሩ ሁሉ በጣም ደስ ብሎአቸው ነበር::ፕሮፌሰሩንም  የሚቀበለው  ሕዝብ ብዙ ነበር  ::  ከአንቦ  ከትውልድ ቦታቸው እንስቶ እስከ ሐረር  ድረስ  በሚሊዮን  የሚቆጠር  ሕዝብ  ተቀበለኝ ይላሉ:: ይኼ የሕዝብ  ማዕበል  ናላቸውን  አዙሮ ያሰከራቸው ይመስለኛል።  በኢትዮጵያ  ዲሞክራሲያዊ  ሥርዐት መዘርጋት  የሚለው  ዓላማቸው ቀርቶ  ሀሳባቸው በመሠረቱ የተቀየረ ይመስለኛል። 

በኢትዮጵያውያ ውስጥ የለውጥ ሂደቱን በተመለከተማለትም ዶክተር  አብይ ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ  ያደርጉትን አንዳንድ ድርግቶች እንመልከት::

በአብዛሃኛው  የዉይይት  መድረክ  ላይ ሲታዩ  ፕሮፌሰሩ ተቃራኒ በመሆን ገንቢ ሃሳብ በማቅረብ ፋንታ የውይይቱን  ጽሁፍ፡  ላለመፈፀም/ላለመተገበር ፕሮፌሰሩም ብዙ ምክንያቶች ሲተበትቡ ይታያሉ:: 

ለብዙ ዓመታት የአንድ ፓርቲ ልቀመንበር በመሆን አገልግለዋል :: በተጨማሪም የፖለቲካ መምሕርም ናቸው::  በግልፅ ቋንቋ”  ሲነገር ስለኢትዮዽያ በቂ እውቀት አላችው ብዬ እምናለሁ:: ያላቸውን ሀሳብ በግልፅ ቋንቋከተናገሩ ከአብዛኛው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚያጣላቸው ስለሚሆን ከልባቸው የሚያስቡትን ለመናግር   አይፈልጉም የሚል ጥርጣሬ አለኝ::

ጠቅላይ ምንስቲሩ ለሹመት የሚያቀርቡትን ሰዎች አናፀድቅም ሲሉ ተሰምተዋል:: ለምሳሌ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለምርጫ ቦርድ ለሊቀ መንበርነት ሲሾሙ ተቃውመው ተቋውሟቸውም እንድመዘግብላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል::  

የፕሮፌሰሩ ተቃውሞ በብርቱካን ሚዴቅሳ ችሎታና ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ከዚያ በኋላ ምርጫ ቦርድ ላይ ለሚያቀርቡት መመሪያዎች  የክስ ነጥብ ምዝገባ መጀመራቸውን የሚያሳይ ድርጊት ነበር።  ብርቱካን ሚዴቅሳ  ፕሮፌሰሩን በሚያሳፍር መልክና ችሎታቸውን በሚያስከብር ሁኔታ ለዓለም ሕዝብ አሳይተዋል።  ፕሮፌሰሩ በምርጫ ለምን እንዳልተሳተፉ የሚያቀርቡት ምክንያቶች በቂና አሳማኝ አይደሉም። ከምክንያቶቹም  ጥቂቶቹ   ምርጫ ቦርድ አይታመንም፤ ምርጫ አስፈፃሚና ታዛቢ ብለው የላኩልን ሙያአቸው ሲታይ አንዳንዶቹ ኤለክትሪሻን፣ መንገድ ጠራጊ፤ እንጨት ፈላጭ ወዘተርፈ እያሉ ምርር ብለው ሳያፍሩ ደጋግመው ሲናገሩ ተሰምተዋል። ማንም ኢትዮጵያዊ እንደሚያቀው እሳቸውንም ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች በሥራ አጥነት ይኖራሉ። ከነዚህ ሥራ አጦች  መሀል አንዳንዶቹ  እሳቸው ፕሮፌሰር የሚጠሉትን ሥራ ቢሠሩ ያስመግናል እንጂ የሚያስወቅስ አደለም። ፕሮፈሰሩ ማዕረግ መሸከም እንጂ ሰለሥራ ያላቸው አስተሳሰብ በጣም ኋላ ቀር ነው።

አሜሪካን አገር መጥተው ዶላር ተሸክመው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ገንዘቡን ያዋጡላቸው ሰዎች የተለያየ ዲግሪ ያለቸው የተለያየ ሥራ የሚሰሩ ከቤት መጥረግ መጀሮ መሆኑን ቢረዱ መልካም  ነው። 

ምርጫን ለማስፈፀም ብዙ ወጣቶችን የምርጫ ቦርድ ሊቀ መንበር ብርቱካን ሚዴቅሳ አሳትፈዋል።  ለነዚህ ወጣቶች ምርጫ ቦርዱ በቂ ሥልጠና እንደሰጠ ተነግሩዋል። ፕሮፈሰሩ በሰዎች ሥልጠና የሚያምኑ አመስሉም።  የሚያስፈራ ባሕርይ ነው። 

፪ኛው ክፍል ለይ ይቀጥላል……