እውነት ማሽነፏ አይቀሬ ነው

October 25, 2021

የኢትዮጵያኖች በአሜሪካ ውስጥ ያደረጉት እውነትን የማሳወቅ ትግል ትንሽ ውጤት እያሳየ ነው:: በመጀመሪያ ላይ ሰበር ዜና ለማለት ፈልጌ ነበር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይኼ ቃል ትርጉም የለሽ ሆኗል :: የውሸት ዜና ዋና ምልክት ሆኗል:: ትልቁ ነገር ለኢትዮጵያውያን ወጌኖቼ ለማለት የፈልግሁት በአሜሪካን አገር በትውልደ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ ይሉታል) የተደረገውና መደረግ ላይ ያለው እውነትን የማሳወቅ ትግል በትንሹ ውጤት እያሳየ ነው::

ለአለፉት በትንሹ ሦስት አሥርተ ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ የተጠነሰሰው ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ የተሳካ እንዲሆን በተደራጀ እቅድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች፤ በተባበሩት የዓለም አቀፍ መንግስታት ድርጅቶች፤ ተያያዥ ቅርንጫፎች ሁሉ ይኼንን ዕቅድ ሥራ ላይ የሚያውሉ ግለሰቦችን ትሰግስገው ይገኟሉ::

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን የሚዲያና የመገናኛ መዋቅሮች ውስጥ የራሱን ዓላማ ሥራ ላይ የሚያውሉ ግለሰቦች አሰልጥኖ በማስቀጠር፤ ከኢትዮጵያ በዘረፈው ገንዘብ ሎቢስቶችን በመቅጠር የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማካሄድ ጥቅምት 25 ቀን 2013 በኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ያካሄደውን የክህደት ጥቃት በመካድ ጠ/ሚአብይ አህመድ ነው ጦርነት የከፈተብን የሚል የውሸት ግንባር ፈጥሮ ነበ::

የዓለምን ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ አሰልፎ   የፖለቲካ ግንባር ቢፈጥርም   ነገሮች መቀየር ጀምሯል:: እውነቱ እየወጣ ነው:: በአለፈው ሐሙስ በ10/21/2021 በፈረንጆች አቆጣጠር የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭው ጉዳይ ኮሚቴ ያሳለፈው ሪዞልሽን አሜንድመንት (amendment 445)  አዲስ ነገር ባይኖረውም (አሰልቺና ተደጋግሞ የሚነግር ስልለሆ ነ) በአዎንታ መታየት ያለበት  ኮንግሬስ አባል የሆኑትና ሬዞሉሽኑን የመሩት   ካረን ባስ  ሕጉ ካለፈ በሁዋላ የሰጡት አስተያየት ሰበር ነው::

ለመጀመሪያ ጊዜ በሥልጣን  ሃላፊነት ያሉ መሪ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት የተጀመረው በትግራይ ተዋጊ ግንባር በሰሜን የኢትዮጵያ ዕዝ ላይ በደረገው ጥቃት መሆኑን ካረን ባስ  አብስረዋል:: ይኼ በዲያስፖራው ማለትም በውጭ ባሉት ኢትዮጵያውያኖች የተካሄደ የትግል ውጤት ነው:: እንኳን ደስ አለን ማለት ተገቢ ነው::

ካረን ባስ  ያበሰሩት እውነትን ነው፤ የአቁዋም መግለጫ ውስጥም ባይገለጽም :: ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል:: ለኮንግሬስ አባሉዋ ካረን ባስ የምስጋናና የማበረታቻ መልዕት መላክ ተገቢ ነው :: ትናንሽ ድሎችን ማስተዋል (recognize) ማድረግ መቻል አለብን።

ትግሉ ይቀጥላል።