ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና "በግልፅ ቋንቋ" ክፍል ፪
ጥቅምት 24 2014
ፕሮፈሰር መረራ ጉዲና አሜሪካን አገር ለማስፈፀም የመጡበትን ጉዳዮች እንደፈለጉት/እዳሰቡት ሊያሳኩ የቻሉ አይመስለኝም:: ያሰቡት አንደኛውና ዋነኛው በኔ ግምት ለራሳቸውና ለድርጅታቸው ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ)… አሁንም ድርጅቱ ካለ?.. ከለሌም ለራሳቸው ገንዘብ ለመለመንና/ለመሰብሰብ ነው። ይኼ ዕቅድ እዲሳካ እስካሁን ቢያንስ 12 የአሜሪካን ከተሞችን ጎብኝተዋል።
የገንዘብ አሰባሰቡን መሳካት የኦሮሚያ ትንሿ ሪፑፕልክ ብለው በሚጠሩዋት በሚኔሶታ የተደረገላቸውን ቀዝቃዛ አቀባበል መመልከቱ ይበቃል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የሰዎች ቁጥር ከመቶ በታች መሆኑን አንዱ የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጓደኛ ነግሮኛል። ይኼ የሚያሳየው በሁለተኛዋ የኦሮሞ ሪፓብሊክ (በእሳቸው ገለፃ ነው) የተቀበላቸው ሰው በጣም አነስተኛ መሆኑ ፤ በሌሎች የአሜሪካ ከተሞችም የተደረገላቸው አቀባበል ቀዝቃዛ መሆን እንደሚችል ማሳያና ጠቌሚ ሊሆን ይችላል:: ሆኖም ለብሔርተኛ ፖልቲካቸው በቂ የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አግኝተዋል ብዬ እገምታለሁ::
ሌላው የገንዘብ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ማወቅ አይቻልም:: የውጪዎቹ ደጋፊዎቻችን ተደራደሩ ይሉናል የሚሏቸው መንግሥታትና ግለሰቦች የሚሰጧቸውን የገንዘብ መጠን ከሺዎች እስከ ሚሊዮን ዶላሮች ሊድርስ እንደሚችል መገመት ይቻላል:: ፕሮፈሰሩ ሚኔሶታን ሁለተኟ የኦሮሚያ ሩባብሊክ ሲሉ አንደኟዋን የኦሮሚያ ሩባብሊክ ለመመስረት ብዙ ገንዝብ እንደሚያስፈልግ ያውቃሉ:: የገንዘብና የእርዳታ መጠን የትልቋን ኦሮሚያ መመስረቻ ቃል የተገባላቸው ይመስለኛል:: ኢትዮጵያ ከተመለሱ በሁሗላ የሚካሄደውን ጦርነት ለመፍታትና ሰላም ለማስፈን የሰጡት መግለጫና የመፍትሄ ሃሳቦች ላለፉት ቢያንስ 11 ወራት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚጥሩ ከተወሰኑ የውጭ አገር መንግሥታት ሃሳቦች ጋር ይመሳስላል::
ይች አህያ ወርቅ ተጭና መምጣቷ …ለመደርምስ ይሆን? የኢትዮጵያ መከላከያን ያጠቁ አገር ካሃዲዎች ማለትም ሕወሐትና ኦነግ ሽኔን ፣ ሌሎች ወንጀለኞችንም ያቀፈና “በገለልተኛ ተቋም ስም ” ( ማለት “የውጭ ሰዎች” በሚመሩት) የጋራ ውይይት ጥሪ አቅርበዋል። ይኼ ገና ከጅምሩ የተጨናገፈ ነው። አሜሪካኖች የሚሉት “ነን ስታረተር” ነው። እሳትና ደረቅ ጭድ አንድላይ ማስቀመጥ ነው። ውጤቱ ቃጠሎ ነው። አመድ ነው። ይኼ በቅንነት የቀረበ ሀሳብ አይደለም። ፕሮፈሰሩ ልማዳቸው ነው። በአለፉት ሦሰት ዓመታት ገንቢ ሀሳብ ሲያቀርቡ ትዝ አይሉኝም። በግልፅ ቋንቋ ፕሮፈሩ ከሚስተር ፈልትማን የአሜሪካው ተወካይ ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያቀዱት ሴራ ነው። ኢትዮጵያን የነካ የለው ፋይዳ። መንገዱን ጨርቅ ሳይሆን የገሃነሙን ያድርግሎት።
ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!