የኢትዮጵያ 6ኛው አገራዊ ምርጫ በሰኔ 14 ሰኞ ሊካሄድ ሕዝቡ እሁድ እኩለ ሌሊት ላይ በመሰለፍ የምርጫ ሰዓት መድረስን ሲጠባበቅ ማየቱ፣ ቀኑን ሙሉ ረጅም ሰልፍ ላይ ቆሞ በፀሐይና በዝናብ ደከመኝ ሳይል በትእግስት ተራውን ጠብቆ አንዳንዱ ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ቆይቶ በመምረጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነቱን፣ ትዕግስቱንና ለዴሞክራሲ ያለውን ጥማት በተግባር አሳይቷል። ዐይን ላለው ለሚያይ፣ ጆሮ ላለው ለሚሰማ የምርጫው ሂደት በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው።
ይኼ የሰኞ ሰኔ 14 ቀን የምርጫ ሂደት በጣም ብዙ ነገሮች የታዩበት ምርጫ ነው። በመጀመሪያ የምርጫ ቦርዱ ከመንግሥት ገለልተኛ መሆኑ የታየበት፤ ምርጫውን ማስተባበሩ በአገር ደረጃ ምን ያህል ከባድና ፈታኝ እንደሆነ ያሳየበት፤ አገሪቱ ባለችበት የፀጥታ ሁኔታ ይኸንን ምርጫ ማከናወኑ፤የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የዳበረና ባለሙያ (professional) ተቋም መሆኑ የታየበት ጊዜ ነው። ምርጫ ቦርዱ እንደተቋም ከነጉድለቱ ጥሩ ሥራ በመሰራቱ መመስገን ይገባዋል፡ ሰህተቶችይታረማሉ።
እዚህ ላይ አንድ ነገር መጥቀሱ ተገቢ ነው፤ ከምርጫው በፊት ከዋሽንግተን አመሪካ እስከ አዲስ አበባ ድረስ የተለያዩ ሚዲያ ነን ባዮች ምርጫ ቦርዱን በመጥፎ ገፅታ ለማሳየትና ተቀባይነት እንዳይኖረው ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልዋሹት ውሸት የለም። ምርጫ ቦርድ በምርጫ ቀን አዋረዳቸው። በምርጫው ቀን በቀጥታ የተለያዩ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የሚስተላልፉትን ሥርጭት በምስልም ሆነ በቃል የሚታይና የሚሰማ ተዘናግተን እናሞኛችሁ በማለት ኢትዮጵያውያ ውስጥ የሚነውን እያቀረቡ ከሚታየውና ከሚስማው ተቃራኒ ኢትዮጵያውያንና ምርጫ ቦርድን ለማሳነስ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ። ፈረንጆች ይኼንን ድርጊት pathetic ይሉታል።
◦ በሴ 14 ቀን ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነትና ትዕግስተኛነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃ መሆኑን በአደባባይ በደንብ ያስመሰከረበት ቀነ።
◦ የተለያዩ ጋዜጠኞች ትልቁን ትንሹን መራጭ ሲጠይቁ፣ ግለሰቦች መልስ ሲሰጡ ማየት በጣም ደስ ይላል፣ የመንግሥትና የግል ሚዲያ እኩል ሲሳተፉ ማየቱ ደግሞ የበለጠ ያረካል።
◦ ሌላኛው በሰኔ 14 የታየው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጨዋነት (maturity) ነው። ሁሉም ፓርቲዎች ያሳዩት ሃላፊነት በጣም የሚደነቅ ነበር። ምርጫው በሰላም እዲጠናቀቅ ክፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል።
◦ የኢትዮጵያ መንግሥትም ፀጥታን በማስከበር ምርጫው በሰላም እዲከናወን ሀላፍነቱን ተወጥቷል
◦ ኢትዮጵያውያ ላይ የተጋረጠው የውጭ አገራት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችና እገር ውስጥ ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ማለትም ምርጫው እንዳይካሄድ ከሚፈልጉት ጋረ በመናበብና በመተባበር የሰኔ 14 ቀን ምርጫ እዲከሽፍከፍተኛ ዘመጃ መካሄዱ የማይረሳ ነው። ሆኖም ኢትዮጵያውያ አሸንፋለች። ምርጫውን አጠናቀናል፣ የግድባችንም ውሀ ሙለት ይካሄዳል፣ ሱዳንም ከመሬታችን ለቃ ትወጣለች።
ኢትዮጵያውያ በልጆቿዋ ሃይል ትከበራለች!!
ሀገር ወዳድ::