Hager Wodad Los Angeles
ሀገር ወዳድ ሎስ አንጀለስ
ምንድን ናቸው? የፖለቲካ አክቲቪስት ናቸው ወይስ ጋዜጠኛ /ጁርናሊስት ናቸው?
ዴሞክራሲ ቱዴይ (Democracy Today) የሚባል ትቪ ላይ ቀርበው በዚህ ሳምንት በትግራይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባካሄደው የአየር ጥቃት በጣም እርግጠኛ ሆነው ጥቃቱ የተካሄደው ሲቪሊያንን ኢላማ አድርጎ ነው ይላሉ:: ለዚህም መረጃቸው ገበያው ላይ የሚታዩ ሰዎች የወታደር ልብስ አለመልበሳቸው ነው ይላሉ።
እዚህ መደምደሚያ ላይ እንዴት ደረሱ? የሕወሓት ተዋጊዎች ሸሽተው ጫካና ሕዝብ መሀል ከተበተኑ በኃላ የሚቀሰቅሱት የሲቪል ልብስ ለብሰውም ነው።
ገበያው ላይ የሚታዩት በርግጥ ሲቪሏውያን ናቸው ወይ? ወይዘሮ ፀዳለ ግን እርግጠኛ ሆነው ነው የሚናገሩት።
ሌላ የሚገርመው ደግሞ ወይዜሮ ፀዳለ በዘገቯቸው ሁለት መከላከያ ሃይል ፤ሁለት መንግሥት እያሉ ሲያወሩ ይኼ ዕውቀት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ አይደለም። ከጋዜጠኝነት ይልቅ ወገንተኛ መሆናቸውን በግልጥ ስለጦርነቱ አጀማመር በማድበስበስ የተናገሩት ሕወሀት ነፃ ሲያደርጉ ይታያሉ።