June 26, 2021
የኢትዮጵያ ጉዶች::
አንቺ ኢትዮጵያ የማትወልችው ጉድ የለም። እንደ አጋጣሚ ዩቱብ ስከፍት ቴሌቪዥኔ ላይ የሚታየው ኢትዮ 360 የሚል ነው። አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ ላንቃው እስከሚሰነጠቅ ሲጮህ አየሁና ቁጭ ብዬ ማየቱንና ማዳመጡን ጀመርኩ። የሚያወራው ባልደራስ ያሚባል ፓርቲ ለምን አዲስ አበባ ውስጥ እንደተሸነፈ ነው፤ ብዙ ምክንያቶችን ቢያትትም ሁለቱ 1) በመጀሪያ ምርጫው ተበልቷል ብሎ ስለአመነ 2)እስክንድር ስለአልተመዘገበ እያለ ብዙ ምክንያቶችም ጨምሮ ይዘረዝራል::
ይቀጥልና በአመሪካን አገር የምርጫ ሂደት ለፕሬዚዳንት፣ ለሴኔትና ለኮንግረስ እንዴት እንደሚካሄድ ሲያስረዳ ብዙ ጊዜ ያባክናል። ይኼ ሁሉ አላስፈላጊ ነው :: ዓላማው ይመስለኛል ምን ያህል አዋቂ እንደሆነ ለማሳየት፣ ከጀርባው ብዙ የተደረደሩ መጻሕፍት ይታያሉ። የኢትዮጵያ ምርጫ ፓርላሜንተሪያን ነው… ማለትም ተመራጮች ፓርቲዎችን ይወክላሉ። እንግዲህ ከዚህ በፊት እንደሰሰማሁት ከሆነ ኤርሚያስ ለገሠ ዋቅጅራ በአሜሪካ አገር የባልደራስ ወኪል እንደሆነ ነው የማውቀው።
ይኼ የሚወስደኝ ኤርሚያስ ለገሠ ዋቅጅራ በ360 ሚዲያ ላይ እንደገልልተኛ ተንታኝ ሆኖ መቅረቡ… እራሱ ዳኛ …እራሱ ፈራጅ ኢትዮጵያውያኖች አንደሚሉት መሆኑ ነው::
በመጨረሻም የተገነዘብኩት ይኼ ሰውዬ ኢትዮጵያውያ ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሳ የሚፈልግ ይመስላል። ይኸንን ያለኩበት ምክንያት ባልደራስና ሌሎቹ ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን እንዳይቀበሉ ይገፋፋል። የሰማሁት ይኼ ሰው ቁጥር አንድ የሕወሓት ካድሬ አንደነበር ነው። የየሚታመን ነው ወይ? እንግዲህ ኢትዮጵያውያ የማትወልደው ጉድ የለም የምለው ለዚህ ነው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያውያን ከማይታመኑ መልክተኞች ይጠብቃት።
◦