ኢትዮጵያውያን የመበታተኑ ሴራ በሰፊው ቀጥሏል።በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፈኮ) አና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በትብብር የኦሮሚያ መንግስት ማቋቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ይኼ የፖለቲካ ሂደታቸው በግልፅ የሚያሳየው ከትግራይ ብሔርተኞች ጋር በመናበብ በትግራይ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ በኦሮሚያ ውስጥ ለመድገም የታቀደ ሴራ ነው። 

አላማው ጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀውስ ለመፍጠር ነው።አንደሚነገረውም ከሆነ በቀውሱም ምክንያት/ሰበብ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ከአሜሪካኖች ጋር አሾክሹከው የጠነሰሱትን ሴራ ወይም እቅድ ሥራ ላይ ለማዋል ነው ። በዚህም አካሄድ ከሁለቱ አንዳቸው የበላይነት መሪነት ቦታ ለመያዝ ነው።

እስከዛሬ ድረስ ታሪክ የሚያሳየው አቶ ዳዊት ኢብሳ መሪ ካልሆኑ ተቀናቃኛቸውን ከድርጅታቸው ማባረር ወይም ጠንከር ካለ ደግሞ ማጥፋት ነው።

ፕሮፌሰሩም ቢሆን በጣም ተሳስተዋል። ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፣ለሰው ልጅ እኩልነት ሲሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሁሉንም ኢትዮጵያውያኖች መብትና እኩልነት ማለታቸው ይመስላቸው ነበር። በተለይ የኦሮሞ መብት ማለታቸው ግልፅ አልነበረም።

ዛሬም የተካኑት ቀረርቶ፡ ማለት ብሔራዊ መግባባት ፤ብሔራዊ ሸንጎ፤ ብሔራዊ ዕርቅ፤ ወዘተርፈ… ማለታቸው ደግሞ በኪሳቸው የሸጎጧትን ቅልጥ ያለ ብሕርተኝነት በአደባባይ አውጠተው የኦሮሞ ንጉስ አርጉኝ እያሉን ነው። የአቶ ዳዊትን አቛም እንደሆነ ሕዝብ ያውቀዋል። የሰሞኑን የመርጫ ሂደት ደወል ያበሰረውን አዲስ ዘመንና የሕዝቡን ስሜት ሁለቱም ፖለቲከኞች የተገነዘቡት አይመስሉም ። 

ይኼ ድርጊታቸው የኦሮሞን ሕዝብ ይጎዳል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይጎዳል ። ከወያኔ ጋር ሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ለማፍረስ ከሆነ አይሳካላችሁም!

ኢትዮጵያውያ ለዘለዓለም ትኑር!!