አሁን ወደ ቨኔሳ ፀሃዬ (Vanessa Tsehaye)
የአሁኑ/የዛሬ ስሟ ሲሆን የልጅነት ስሟ ግን ቨኔሳ በርሄ ነበር ። ቨኔሳ በርሄ የስዊድን ዜጋ ናት። በእስዊድን ከሚኖሩ ኤርትራውያን ቤተሰብ የተወለደች ናት።
ቨኔሳ በርሄ አምስት ዓመት ሲሞላት አጎቷ ሥዩም ፀሃዬ ኤርትራ አሥር ቤት ውስጥ መሆኑ ተነገራት። ይኼንን ከሰማችበት ቀን ጅምሮ አጎቷን የማስፈታት የኑሯዋ ዐላማ አደረገች። አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በነበረች ግዜ ገንዘብ በማሰባሰብ አጎቷን ለማስፈታት ያደረገችው ጥረቷ አልተሳካም፤ ሁኔታውም አልፈቀደም ነበር።
ቨነሳ ፀሃዬ ብላ እራሷን መጥራት የጀመረችው በፈረንጆች አቆጣጠር በ2018/2019 አካባቢ ይመስላል። ቨኔሳ ፀሃዬ ዕድሜ ልኳን የኤርትራን መንግስት ስትቃወም የኖረች አክቲቪስት ናት ።
በዐቢይ ኖቤል ሽልማት ላይ ትልቅ ተቃውሞ አቅርባለች። ለኤርትራ ሕዝብ ነፃነት አያመጣም ኢሳያስን ያጠናክራል በማለት ይመስላል። ሆኖም ግን በማይታወቅ ተአምር በNovember 2020 ቨነሳ ፀሃዬ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መሪ ሆና ተሾመች። ይኼ ምን ማለት ነው? ይኼ እንዴት ሊሆን ቻለ?
አንዱ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ግንባር ቀደም ዓላማው በሁኔታዎች ላይ አድሎ አለማሳየት “urgency of impartiality” የሚል መርሆ ሲሆን ፤እዚህ ላይ እንዴት አድርጎ ነው አድሎ አለማሳየት የሚቻለው?
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ድርጅትና አምነስቲ ኢንተርናሽናል አብረው ስለሚሰሩ፡ ማለትም ታላቅና ታናሽ ፡ የአንዱ ግመገማ ለሌላኛው ድርጅት ስለሚያገለግል፤ የቨነሳ ፀሃዬ የቅፅበት ሹመት በጣም የሚያጠያይቅ ነው።
ቨነሳ ፀሃዬ ምን ያህል ገለልተኛ መሆን ትችላለች? ኢሳይያስንና አብይን ትቃወማለች።
በትግራይ የተደረጉት ሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት አቀነባባሪ ቨኔሳ ፀሃዬ ናት። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት የሚጠቁመው ይሄንኑ ሪፖርት ነው። ቨኔሳ ፀሃዬ የአክሱምን ጭፍጨፋ ሪፖርት ያቀነባበረች ናት።
በኢትዮጵያ ላይ የተጠነሰሰ ሴራ ያለ ይመስላል። የተባበሩት መንግስታት ቅርንጫፍ ድርጅቶች በሙሉ የተሞሉት ኢትዮጵያውያንን ለማንበርከክ ከአመሪካ መልእክት የተቀበሉ ይመስላሉ። ስለዚህ ማናቸውም ለኢትዮጵያ ጥሩ ነገር ያስባሉ ብሎ አይታመንም።
ማንም የሚያየው ነገር ቢኖር ቨኔሳ ፀሃዬ (በርሄ) ፅናቷዋና ለቆመችለት ዐላማ የከፈለችውን ዋጋ ነው።