መልዕክት… ውጪና አገርቤት ላሉ ኢትዮጵያኖች በሙሉ።

ዶክተር አቢይ ወደ ሥልጣን እንደመጡ አንዱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡት ቃል መገናኛ ብዙሃንን (ሚዲያዎችን) ነፃ ማድረግ ነበር። እስካሁን ድረስ ዶክተር አቢይ ይኼንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የገቡትን ቃል አክብረዋል። ማንበቡን ስትቀጥሉ ይኼ ሀሳብ ግልፅ ይሆናል። 

እስካሁን እደሚታየው የግል መገናኛ ብዙሃን ትንተና ከአገር ገንቢ ሀሳብ አንስቶ እስከ አገር አፍራሽ የሆኑ ሀሳቦችን ሲያቀርቡ ይደመጣሉ። አንዳንዶቹ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ብሔር ተኮር ናቸው።በተለይ የክልሎቹ ። ሌሎችም የግል የሆኑ ብሔር ተኮር የሆኑ አሉ/ነበሩ።

ኢትዮጵያውያ ውስጥ ዋልታ ረገጥ ሀሳቦች ላለፉት ሦስት ዓመታት እንደልብ ሲቀርቡ ሲለፈፉ ሲተቹ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹ አስተያየቶች ለሰው ልጆች ሕይወት መጥፋት፡ ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል። አንዳንዶቹ ሃሳቦች የኢትዮጵያኖችን ህልውና በማደንዘዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ ለመቀልበስ ሌት ተቀን ሲታታሩ ይታያሉ። 

ሁለቱን ማለት ኢትዮ 360ና የትግራይ ቴሌቪዥን / የትግራይ ሚዲያ ሐውስን እንጥቅስ። የሁለቱ ዐላማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ለውጥ እንዳይሳካ ማድረግ ነው። አመጣጣቸው ከሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች ነው። የትግራይ ቴሌቪዥን / ትግራይ ሚዲያ ህዋስን ማስረዳት አያስፈልግም። ምክንያቶቹ ግልፅ ስለመሰለን። የኢትዮ 360ን ለማስረዳት የሚከተሉትን እንይ። 

ለአለፉት አመታት ከኢሳት ተገጥለው እራሳቸውን ኢትዮ 360 ብለው መጠራት ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ(አራት አቅራቢዎች) ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው የኢትዮጵያውያን ዜጎችን እርስ በርሳቸው እንዲጠራጠሩ ሰፋ ያለ ሥራ ሰርተዋል። ኦሮሞው አማራውን፡ አማራው ኦሮሞን እንዳያምን የጥላቻ መርዝ ረጭተዋል። በትግራይ ያለው የትግራይ ቴሌቪዥን / የትግራይ ሚዲያ ሐውስ ዶክተር አብይን አሃዳዊ ጨፍላቂ እይያሉ ሲግልፁ፡ የ360ዋ እንስት ደግሞ የኦሮሙማ የበላይነት አደጋ ኢትዮጵያውያ ላ መጥቷል እያለች ሁለቱም አንድላይ በመሆነ በየአቅጣጫው የሚስብኩት ሁለት ወይም ሦስት ግቦችን መቶላቸዋል። 

በግንባር ቀደምትነት እነዚህ ግለሰቦች ሁሉንም የለውጡ ሪፎርሞችን በኦሮሙማ መነፅር በማየት ሥራቸው መቃወም ወይም ማቀርሸት ነው።የሚሊታሪ ሪፎርም፣ የፍርድ ቤቶች፣የምርጫ ሕግና የምርጫ ቦርድ መዋቅር… ወዘተ የመሣሠሉትን ለውጦች ባልተሟሉ መረጃዎች ፤ አንዳንዴ ደግሞ ከኪሳቸው ባወጡት መረጃ የሚመስል ግን ፍብረካና/ልብ ወለዶችን በመጠቀም ለውጦቹን በሙሉ የኦሮሙማ ጥላሸት በመቀባት ነው። 

ሌላው ድርጊታቸው ደግሞ ተቃዋሚ ነን በሚል ሰበብ የዶክተር አቢይን መንግሥት የሚቃወሙትንና ኢትዮጵያውያን ለማፍረስ በሚጥሩ የሚታወቁ ግለሰቦችን በመጋበዝ “ኦሮሞ መጣብህ ” የሚለውን ሆይሆይታ ማስተጋባት ነው። 

ይኼ ሁሉ የሚደረገው ደግሞ ዋሽንግተን ዲሲ እስቱዲዮ ውጥ ቁጭ ብለው ነው። ቀንደኛ/አውራ የሚመስልው ሰውዬ ደግሞ መጽሔት ከጀርባው በመደርደር አዋቂነቱን ለማሳየት በሚመስል ይሄ ማትስ 101 ነው፡   ይሄ ኢኮኖሚክስ 101 ነው ይሄ ሳይኮሎጂ 101 እያለ በዚያን ቀን በሚያወራው አርእስት የዶክተር አብይን አለማወቅ ለማሳየት ሲሞክር፡  ከዚህ በኋላ ሁሉም ባንድ ላይ ዶክተር አቢይን እንደተራ ሰው ክቡሩን በማሳነስ፤እንደተራ መንገደኛ መምራት የማይችል ፡የዞረበት፤ አገሪቱ  መሪ የሌላት እያሉ ተራ በተራ የአስተሳሰባችውን ክብደት በሚመዝን/በሚያጋልጥ ቃላቶችን ሲቀባበሉ ይታያሉ። ልጅቷም ዶክተር አብይን ለማጥቃት በሚል ይመስላል የሰውን ህሊና በሚያስክፉ ቃላት ጥያቄዎችን ታቀርባልች።ይሄ በኢትዮ 360  የሚታይ የየቀኑ ከኣማኑኤል የሚላክ መልክት ነው።  

ይኼ ሁሉ የሚደረገው ለአማራው ሕዝብ ጥብቅና መቆም በሚል ነው። አውራው በአለፉት 15ና 20 ዓመታት የአማራን ሕዝብ ያስጠቃ ፡ንሰሃ ምን መሆኑን ያልተረዳ ስለሆነ ሕብረተሰባችን አፍ ከመያዝ ምን ይበል? አማራውን ብቸኛ የማድረግ አባዜም ከመቀሌም የሚሰማ ጩሄት መሆኑንም ይገነዘብ ይሆን?

አሳዛኙ ግን ኢትዮጵያውያ ውስጥ ብዙ ወጣቶች በዚህ በሚዲያ ሥራ የተሰማሩ ተስፋ የሚጣልባቸውና ችሎታቸው በደንብ የሚታይ ሆኖ ሳለ አንዳንዶቹ ግን በኢትዮ 360 ቫይረስ የተበከሉ ይመስላል። ለምሳሌ አውድማ ፕሮግራም ጥሩ ሆኖ ሳለ ወጣቶቹ የግድ ጥሩውን ነገር ለማፍረስ የግድ ድንጋይ መፈንቀል ያለባቸው ይመስላቸዋል። በነገራችን ላይ አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ  ሀሳብ ለመስጠት ደግሞ ሦስት ሰዎች አያስፈልጉም። 

በሦስተኛ ደረጃ አመሪካ ውስጥ እንዲህ ዓይነት እንደ ኢትዮ 360 ሚዲያ ያሉት የገቢ ምንጭ መሆናቸውን አንዘንጋ። የግለሰቦችን ስሜት ቀስቅሶ ፡አስለቅሶ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ባልተረጋገጠ መrvጃ “አሁን የደረሰን” በሚል አስደንጋጭ መልክት ገንዘብ መሰብሰብ ነው።

እንደኛው እኛ በበጎ ፈቃዳችን የምንገብረው ሲሆን ፡ “ያቺን ደወል ስንጫን” ዩቱብም ዶላር ይከፈላቸዋል።  የሚጮሁት ታዲያ ለምን መሰላችሁ? አረንጓዴው ዶላር እየታያቸው ነው። በልባቸው እየሳቁ ዶላርዋን ይዘው ወደ ባንክ ቤት ይሮጣሉ።   አንዳንድ ቀን ዛሬ ብዙ ተመልካች አለን ብለው የሚደሰቱት ለምን እንደሆነ ይገባችኋል። 

የነዚህ ታሪክ ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም። እስክንድርን/ባልደራሰን አብንንም ሲጠቀሙ ይታያሉ። እይታውና አካሄዱ ጀርባዬን እከከኝ ጀርባህን ልከክልህ ይመስላል።

አብዛኛውን ጊዜ ሲመፃደቁ ይሰማሉ።  “የዛሬ ሁለት ዓመት” “የዛሬ ዓመት” እያሉ ጊዜ በመቁጠር “ለአብይ ነግረነው ነበር” ሲሉ ይሰማሉ። የዶክተር አቢይን ፖሊሲ አንድም ቀን በእውነት ሲናገሩ አይሰሙም። 

አንዱማ ለዶክተር አቢይ የለውጥ ሮድ ማፕ ሰጠሁ ያለው እስር ቤት ነው። እነዚህ ደግሞ  እሱን መተካታቸው ይሆን? አስር ቤት ያለው ኦሮሞን አነሳስቶ አማራ ላይ እዲዘምት ነበር። እነዚህኞቹ ከመቕለ ጋር በመናበብ  ላለፉት ዘመናት ያካሄዱትን እንደገና ለማካሄድ ማለት አማራው ከኦሮሞ እንዲጋጭ ሙከራ እያደረጉ ነው። አንሞኝም … ነቅተናል እንበላቸው። 

በተለይ ምዕራባዊያን በአሜሪካ መሪነት አገራችን ላይ እየተካሄደ ያለውን  “የወያኔን ግርግር” በመጠቀም የጎነጎኑትን ሴራ ለማከናወን የዘመኑ “ጫላቢዎች” ማለትም በሻለቃው በዳግመ ልደትና ባንድራ አጃቢን በማሰለፍ ኢትዮጵያ ለመግባት የተዘጋጁ ይመሰላሉ። 

እስከአሁን ያየነው የኢትዮ 360 ባሕሪይ  ዐላማውና ጠባዩ የአቢይን መንግሥት መገልበጥ ወይም ማስገልበጥ ሲሆን ፡ እግረመንገዳቸውንም በአረንጓዴ ዶላር መክበር ነው። ውጭ ላለነው የሚታየን ግምት ስለሆነ አገር ውስጥ ካላችሁትም አንጋራው ብለን ነው። 

ቸር ይግጠመን!