ይድረሰ ለተከበሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ኣህመድ

ሚያዝያ 6 2014.         April 14 2022

                            ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህምድ ዶ/ር

 

ለክቡርነትዎ በዚህ አጭር ደብዳቤዬ ደጋፊዎ እንደመሆኔ መጠን አንድንድ በጣም የሚያሳስቡኝ ጉዳዮችን ለማንሳት እሞክራለሁ። ሀሳቦቼን ከመግለጼ በፊት እርሶም ሆነ ሌሎች ይኼንን ጽሑፍ የሚያነቡ ሰዎች እንዲያውቁልኝ የምፈልገው እንደግለሰብ እርሶዎ ወደሥልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄዱትን ለውጦች በማድነቅ፡ አመራሮም በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያ አስፈላጊ እንደሆነም የምረዳ ግለሰብ ነኝ ። በየጊዜው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡት አስተያየቶች/ መመሪያዎች አመርቂና ደስ የሚሉ ራዕይ ያላቸው አገር ገንቢ መሆናቸውንም እገነዘባለሁ።

ስልጣን ላይ እንደመጡ .ማለትም ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ  የገጠመዎት ችግሮች እርስዎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከገለጹት በላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ አስአቸጋሪ እንደነበረና እንደሆነም እረዳለሁ። በፅናቶም አደንቆታለሁ።።  የተካሄዱትን መዋቅራዊ ለውጦችን፤እንደመከላከያ፣ የደህንነት መዋቅር፣ የፍርድ ቤቶችና የማረሚያ ቤቶች ፣ የምርጫ ቦርድና የምርጫ ሕግ፣ የሚዲያ ተቋማትና የሚዲያ አካባቢ የተደረጉ ለውጦች አመርቂ ናቸው፡እላልለሁ።  አንዳንዶቹም ውጤት እያሳዩ ነው። በኔ ግምት እነዚህ መዋቅራዊ ለውጦች ቋሚ ሆነው የሚቀጥሉ ናቸው ብዬ ተስፋ አዴርጋለሁ።

 እርስዎ ይኼንን ውጤታማ ለውጥ ሲያካሂዱ/ሲመሩ ገና ከጅምሩ በአንፃሩ ለውጡ እዳይሳካ የተሰሰለፉ ኀይሎች እንደነበሩና አሁንም እንዳሉ እረዳለሁ። እነዚህ ኃይሎች በተለያየ ስም እራሳቸውን ቢጠሩም የእርስዎን መንግስት ገና ከጅምሩ ‘አሀዳዊ’ ነው ብለው በመፈረጅ አሁን ላለንበት ቀውስና ችግር አንዲሁም  ለገባንበት/ላለንበት  የጦርነት ሁኔታ አድርሰውናል።

አሁን ወደ ተነሳሁበት  ቁም ነገሮች ልመለስ። እንደሚከተለዉ አቀርበዋለሁ።

  1. በየቦታው ክልሎች ውሰጥ በሚደርሱት መፈናቀሎች ግድያዎች አስተያየት ሳይሰጡ በዝምታ ማለፍዎ፤

  2. ክልሎችን ማስፋፋትዎ፡

  3. ክቡርነትዎ ወደ ሥልጣን እንደመጡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ከዳር እስከዳር እግዚአብሔር ለእስራኤሎች ሙሴን እንደላከው ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላክ እንደላኮት አድርጎ ነበር  የተቀበለዎት….  ወጣቱ፣ ሽማግሌው ፣ ሴት ወንዱም ፡የኢትዮጵያ እናቶችም  በዕንባ አምላክን በማመስገን እርስዎን ተቀበሉ፤ ፀለዩሎት። እርሶም አፀፋውን መለሱ። “ስንወለድ ኢትዮጵያዊያን ስንሞት ኢትዮጵያ” በማለቶዎም ጭምር። እንደቀድሞ የኢትዮጵያ  መሪዎች “አገሪቷን”  ከማለት ፈንታ ኢትዮጵያ እያሉ በስም መጥራት ስለጀመሩ።

  4. በዚህ መሀል ቀስ በቀስ ገና ከጅምሩ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ባንኮች ሲዘረፉ፣ ቀበሌዎች ሲያዙ፣ ሰዎች በዘራቸው ምክንያት ሲፈናቀሉ ሲገደሉ፡ ይኼ ሁኔታ የቀን ተቀን ዜና መሆን ጀመረ። የመፈናቀል የሞት ጥቃቶች ወደ ጉጂም ተዛመቱ። መንግሥትም ይኼንን የሚያደርገው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ነው ሲል ነበር።

  5. የዛሬ ሦስት ዓመት ወይም ከዚያ በፊት ይኼ ሁኔታ በአባ ገዳዎችና በክልሉ መንግሥት እየተፈታ ነው፤ ሊፈታነው ወዘተ…  ቢባልም  የሰዎች በዘራቸው መፈናቀልና መሞት ቀጠለ። የነዚህ ጽንፈኛ ኃሎች መሪ አዲስ አበባ ውስጥ ቁጭ ብለው፡ የልብ ልብ ተሰምቶቿው “ማን ማንን ትጥቅ ያስፈታል” ብለው መፎከር ጀመሩ። ነፃ አውጪ ድርጅት ስሙን ቀይሮ ሸኔ ነኝ ሲል እኝሁ መሪ አላውቃቸውም አሉ። ነገሩ ዓናችሁን ጨፍኑ ላሞኛሁ ሆኖ ተገኘ ። አሁን በሁሉ ኦሮሚያ ተስፋፈተዋል። የኦሮሚያ መንግሥትም ሆነ የፈደራሉ መንግሥት መፍትሔ ማግኘት አልቻሉም።

  6. ዓላማዬ በኢትዮጵያኖች ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ለማተት ሳይሆን ይኼንን ሁኔታ በሚመለከት እርሰዎም ሆነ የክልሉ መንግሥት ዝምታ መምረጣችሁ ነው።

  7. እነዚህ በዘር ተለይተው የሚፈናቀሉትን ሆነ  የሚሞቱትን  እርሶና የክልሉ ኣስትዳዳሪ የሚመሩት የሕዝብ አካል ናቸው። እኔ ደጋፊዎ እንደመሆኔ መጠን ሰዎች ለምን እነዚህ ሀላፊዎች ዝም ይላሉ ብለው ሲጠይቁኝ መልስ አጣለሁ። ምስጢሩ ምንድነው? የርስዎ መናገር ለተፈናቃዮችም ለሟቾችም ቤተሰብ ማጽናኛ ይሆናል የሚል እሳቤ ስላለኝ ነው።

  8. እርስዎ ለሰዎች የርሂራሄ ገፅታ ያሎት መሆኖዎን በብዙ ድርጊትዎ አሳይተዋል። ጨካኝ ሰው አይመስሉኝም።

  9. እንደ ደጋፊዎ የእርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ አለመናገርዎ ከባድ ዋጋ እያስከፈሎት ነው የሚል ግምት አለኝ። አንድ ነገር ያድርጉ።

  10. እርስዎ ወደ ሥልጣን እንደመጡ በአዋሳ ንግግር ሲያደርጉ በንግግሮዎ መሀል ክልል የአስተዳደር ወሰን ነው በማለት ወደፊት እንደሚቀየር አቅጣጫ ያሳዩ መስሎኝ ነበር። ሆኖም ክልሎች በእርስዎ የሥስት ዓመት ዘመን በሁለት ጨምረዋል። ክልሎችን መቀነስ ሕገ መንግሰት ማሻሻል ስለሚጠይቅ መቀየር ወይም መቀነስ ይከብዳል። ማስፋፋት ለምን አስፈለገ? የሚምስለኝ በአገራችን ላይ ብዙ የስደት የሞት የጦርነት ቀጠና ያደረገን የክልል ጉዳይ ነው። መስፋፋት ያለበት አይመስለኝም።   

            የዳስፖራ ደጋፊዎ

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *