Natenael Mekonnen
June 2021
ከሀገር አቀፍ የሰላም ሃይላት የቀረበ ግልጽ ደብዳቤ የተመረጠው የዶክተር አብይ መንግስት ማድረግ ያለበት::
#Ethiopia : አሁን ሁሉኑም ደምሳሽ ሃይላት በአሳማኝ ሁኔታ ሰጥ ለጥ እያደረገ በራሱ መቆሙን እያረጋገጠ የመጣው የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መንግስት የሂደት ለውጡን በልኩ በመመርመር ሊያደርግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ህዝብ በተለያየ መንገድ ሃሳቡን እያዋጣ ይገኛል።
የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ጉዳይ ሊሆን የሚገባው የሰላም ማስፈኚያ መንገዶችን ለህዝባችን በተለያዩ ውሳኔዎች ማረጋገጥ ሊሆን ይገባል። የሰላም ማጣት ዋና ምንጭ የሆነው እና የህዝባችንን የዘመናት ተስፋ በጫንቃው ተሸክሞ እየተመነደገ ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፍፃሜ በፍጥነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ አደናቃፊ ሊሆኑ የሚችሉትን የሱዳን እና ተያያዥ የግብፅ ድንፋታን ለአንዴና እና መጨረሻ ጊዜ ማስቆም ያስፈልጋል። ይህንን ከባድ ውሳኔ ለመወሰን አዲስ ተመራጩ መንግስት ውስጣዊ ሰላምን ማምጣት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን ይገባል።
የትግራይ ጦርነት እና ተያያዥ ጉዳዮቹ በፍጥነት ማብቃት አለባቸው ። በቋፍ ላይ ካሉት የትግራይ ህዝብ ነጻአውጭ ግንባር/ትህነግ ቀሪ ሰላም ፈላጊ አካላት ጋር ድርድር በማድረግ ጦርነቱ በጊዜ ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ መንግስታችን ቆራጥና ተከታታይ የደህንነት ፣ መከላከያና ሰላማዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅበታል። የህዳሴ ግድብ ፍፃሜን ለማረጋገጥ ውስጣዊ ሰላም መፍጠር የግድ ያስፈልጋል። ሱዳን እና ግብፅ ወደ ግልፅ ጥምረት በመሄድ አካባቢያዊ ነውጦችን ለማቀጣጠል ቆርጠው መነሳታቸው ከአለም አቀፍ ወዳጆች ተረጋግጧል። ሱዳን በተለይ የምትባለውን እና የሚነገራትን ትብብር ላይ የተመሰረተ እድገት ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለችም ። የትህነግ አንዳንድ የነውጥ ሃይላትን በማስተባበር ከፍተኛ የጥቃት ዛቻ እና ልዩ ልምምድ ማድረግ መጀመሯም ታውቋል። ከትህነግ አካላት ጋር ሰላም መፍጠር እና የሀገር ውስጥ ደህንነትን በየድርድሩ በማረጋገጥ ከትግራይ ጀምሮ በቤኒሻንጉል ፣አማራ ፣አፋር ፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞች ጋር ድርድር በማድረግ ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን በማቅረብ ውስጣዊ ሰላምን ለህዝባችን ማረጋገጥ ይገባል።
ለባለብሩህ አእምሮው ጠቅላይሚኒስቴራችን ዶክተር አብይ ለመምከር ባንበቃም ያሉት ሀገርወዳድ አካላት አሁን ሁላችንም ይህንን ምርጫ አጠናቀናል መንግስት የሆነው ብልጽግናን በተለያዩ መንገዶች በማገዝ ስራ ሁሉም ሰላም ወዳድ ዜጋ ሊሰማራ ይገባል። ሱዳን እና ግብፅ ግልጽ ሀገራዊ ወቅታዊ ጠላቶቻችን ናቸው ። ሀገር ውስጥ ያለው የትኛውም ሃይል ሰላምን ማስቀደም እና ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባሩ ሊሆን ይገባል።
ሰላም ለትግራይ ሰላም ለኢትዮጵያ፤ የሀገራችንን ሰላም ከተተበተበበት የጥላቻና እልህ ሳጥን አውጥተን በሀገር ዘላለማዊ ፍቅር በማሰዋብ ችግሮችን በድርድር መፍታት እና ሰላምን ማረጋገጥ ባህል እናድርገው! ይቻላል!