PM Abiy Address Ethiopians on Tigray

June 30, 2021

Yesterday PM Abiy addressed the Ethiopian media and groups on why the ENDF forces moved out of Mekele. The main reasons are the ENDF forces were being attacked by the very people they went to protect.

This could only lead to a drawn out and senseless war and breath life into TPLF’s propaganda war and the negative international media coverage of the situation and Ethiopia’s progress.

Hager wodad supports the unilateral cease fire.

The criminal elements (Junta) have been have been crushed, arrested and the remaining ones are on the run. The law and order campaign began on November 4, 2020 and was over in three weeks.

Chasing the low level cadres of TPLF and their forces who discarded their uniform and blended with the people is costly in treasure and blood the nation can’t afford. So far, the eight months war cost $100 billion Ethiopian Birr .

It will also help the Tigrean peasantry to get engaged fully in the farming season at hand.

The seize fire will also give the Tigran people a breather on figuring out on how to govern themselves.

The very people the army went to defend have been caught between a rock and a hard place and PM Abiy has pulled back to have the Tigray people decide their fate while keeping an eye on the remaining junta elements

የዶክተር አብይ መንግስት ማድረግ ያለበት

Natenael Mekonnen

June 2021

ከሀገር አቀፍ የሰላም ሃይላት የቀረበ ግልጽ ደብዳቤ የተመረጠው የዶክተር አብይ መንግስት ማድረግ ያለበት:: 
 
#Ethiopia : አሁን ሁሉኑም ደምሳሽ ሃይላት በአሳማኝ ሁኔታ ሰጥ ለጥ እያደረገ በራሱ መቆሙን እያረጋገጠ የመጣው የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መንግስት የሂደት ለውጡን በልኩ በመመርመር ሊያደርግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ህዝብ በተለያየ መንገድ ሃሳቡን እያዋጣ ይገኛል።

የመጀመሪያው እና ቀዳሚው ጉዳይ ሊሆን የሚገባው የሰላም ማስፈኚያ መንገዶችን ለህዝባችን በተለያዩ ውሳኔዎች ማረጋገጥ ሊሆን ይገባል። የሰላም ማጣት ዋና ምንጭ የሆነው እና የህዝባችንን የዘመናት ተስፋ በጫንቃው ተሸክሞ እየተመነደገ ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፍፃሜ በፍጥነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ አደናቃፊ ሊሆኑ የሚችሉትን የሱዳን እና ተያያዥ የግብፅ ድንፋታን ለአንዴና እና መጨረሻ ጊዜ ማስቆም ያስፈልጋል። ይህንን ከባድ ውሳኔ ለመወሰን አዲስ ተመራጩ መንግስት ውስጣዊ ሰላምን ማምጣት ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን ይገባል። 

የትግራይ ጦርነት እና ተያያዥ ጉዳዮቹ በፍጥነት ማብቃት አለባቸው ። በቋፍ ላይ ካሉት የትግራይ ህዝብ ነጻአውጭ ግንባር/ትህነግ ቀሪ ሰላም ፈላጊ አካላት ጋር ድርድር በማድረግ ጦርነቱ በጊዜ ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ መንግስታችን ቆራጥና ተከታታይ የደህንነት ፣ መከላከያና ሰላማዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅበታል። የህዳሴ ግድብ ፍፃሜን ለማረጋገጥ ውስጣዊ ሰላም መፍጠር የግድ ያስፈልጋል። ሱዳን እና ግብፅ ወደ ግልፅ ጥምረት በመሄድ አካባቢያዊ ነውጦችን ለማቀጣጠል ቆርጠው መነሳታቸው ከአለም አቀፍ ወዳጆች ተረጋግጧል። ሱዳን በተለይ የምትባለውን እና የሚነገራትን ትብብር ላይ የተመሰረተ እድገት ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለችም ። የትህነግ አንዳንድ የነውጥ ሃይላትን በማስተባበር ከፍተኛ የጥቃት ዛቻ እና ልዩ ልምምድ ማድረግ መጀመሯም ታውቋል። ከትህነግ አካላት ጋር ሰላም መፍጠር እና የሀገር ውስጥ ደህንነትን በየድርድሩ በማረጋገጥ ከትግራይ ጀምሮ በቤኒሻንጉል ፣አማራ ፣አፋር ፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞች ጋር ድርድር በማድረግ ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን በማቅረብ ውስጣዊ ሰላምን ለህዝባችን ማረጋገጥ ይገባል። 
ለባለብሩህ አእምሮው ጠቅላይሚኒስቴራችን ዶክተር አብይ ለመምከር ባንበቃም ያሉት ሀገርወዳድ አካላት አሁን ሁላችንም ይህንን ምርጫ አጠናቀናል መንግስት የሆነው ብልጽግናን በተለያዩ መንገዶች በማገዝ ስራ ሁሉም ሰላም ወዳድ ዜጋ ሊሰማራ ይገባል። ሱዳን እና ግብፅ ግልጽ ሀገራዊ ወቅታዊ ጠላቶቻችን ናቸው ። ሀገር ውስጥ ያለው የትኛውም ሃይል ሰላምን ማስቀደም እና ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባሩ ሊሆን ይገባል። 
ሰላም ለትግራይ ሰላም ለኢትዮጵያ፤  የሀገራችንን ሰላም ከተተበተበበት የጥላቻና እልህ ሳጥን አውጥተን በሀገር ዘላለማዊ ፍቅር በማሰዋብ ችግሮችን በድርድር መፍታት እና ሰላምን ማረጋገጥ ባህል እናድርገው!  ይቻላል!


 

የኢትዮጵያ ጉዶች

June 26, 2021

የኢትዮጵያ  ጉዶች::

አንቺ  ኢትዮጵያ የማትወልችው ጉድ የለም።   እንደ አጋጣሚ ዩቱብ ስከፍት ቴሌቪዥኔ ላይ የሚታየው ኢትዮ 360 የሚል ነው።   አቶ ኤርሚያስ  ለገሰ ዋቅጅራ ላንቃው እስከሚሰነጠቅ ሲጮህ አየሁና ቁጭ ብዬ ማየቱንና ማዳመጡን ጀመርኩ። የሚያወራው ባልደራስ ያሚባል ፓርቲ ለምን አዲስ አበባ ውስጥ እንደተሸነፈ ነው፤ ብዙ ምክንያቶችን ቢያትትም ሁለቱ 1) በመጀሪያ ምርጫው ተበልቷል ብሎ ስለአመነ 2)እስክንድር ስለአልተመዘገበ  እያለ ብዙ ምክንያቶችም ጨምሮ ይዘረዝራል:: 

ይቀጥልና  በአመሪካን አገር የምርጫ ሂደት ለፕሬዚዳንት፣ ለሴኔትና ለኮንግረስ እንዴት እንደሚካሄድ ሲያስረዳ ብዙ ጊዜ ያባክናል። ይኼ ሁሉ አላስፈላጊ ነው ::  ዓላማው ይመስለኛል ምን ያህል አዋቂ እንደሆነ ለማሳየት፣  ከጀርባው ብዙ የተደረደሩ መጻሕፍት ይታያሉ።  የኢትዮጵያ ምርጫ ፓርላሜንተሪያን ነው… ማለትም  ተመራጮች ፓርቲዎችን ይወክላሉ። እንግዲህ ከዚህ በፊት  እንደሰሰማሁት ከሆነ ኤርሚያስ  ለገሠ ዋቅጅራ በአሜሪካ አገር የባልደራስ ወኪል እንደሆነ ነው  የማውቀው። 

ይኼ የሚወስደኝ ኤርሚያስ ለገሠ ዋቅጅራ በ360 ሚዲያ ላይ እንደገልልተኛ ተንታኝ ሆኖ መቅረቡ… እራሱ ዳኛ …እራሱ ፈራጅ ኢትዮጵያውያኖች አንደሚሉት መሆኑ ነው::

በመጨረሻም የተገነዘብኩት ይኼ ሰውዬ ኢትዮጵያውያ ውስጥ ብጥብጥ እንዲነሳ የሚፈልግ ይመስላል።   ይኸንን ያለኩበት ምክንያት  ባልደራስና ሌሎቹ ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን እንዳይቀበሉ ይገፋፋል። የሰማሁት ይኼ ሰው ቁጥር አንድ የሕወሓት ካድሬ አንደነበር ነው።   የየሚታመን ነው  ወይ?  እንግዲህ  ኢትዮጵያውያ የማትወልደው ጉድ የለም የምለው ለዚህ ነው።  

እግዚአብሔር ኢትዮጵያውያን  ከማይታመኑ መልክተኞች ይጠብቃት። 

 

ወይዘሮ ፀዳለ ለማ

  ምንድን ናቸው?   የፖለቲካ አክቲቪስት ናቸው ወይስ ጋዜጠኛ /ጁርናሊስት ናቸው?

ዴሞክራሲ ቱዴይ (Democracy Today) የሚባል ትቪ ላይ ቀርበው በዚህ ሳምንት በትግራይ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባካሄደው የአየር ጥቃት በጣም እርግጠኛ ሆነው ጥቃቱ የተካሄደው  ሲቪሊያንን ኢላማ አድርጎ ነው ይላሉ:: ለዚህም መረጃቸው ገበያው ላይ የሚታዩ  ሰዎች የወታደር  ልብስ  አለመልበሳቸው ነው ይላሉ። 

እዚህ መደምደሚያ ላይ እንዴት ደረሱ?  የሕወሓት ተዋጊዎች ሸሽተው ጫካና ሕዝብ መሀል ከተበተኑ በኃላ የሚቀሰቅሱት የሲቪል ልብስ ለብሰውም ነው። 

ገበያው ላይ የሚታዩት በርግጥ ሲቪሏውያን ናቸው ወይ?  ወይዘሮ ፀዳለ ግን እርግጠኛ ሆነው ነው የሚናገሩት።   

ሌላ የሚገርመው ደግሞ ወይዜሮ ፀዳለ በዘገቯቸው ሁለት መከላከያ ሃይል ፤ሁለት መንግሥት እያሉ ሲያወሩ  ይኼ ዕውቀት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ አይደለም።   ከጋዜጠኝነት ይልቅ ወገንተኛ መሆናቸውን በግልጥ ስለጦርነቱ አጀማመር በማድበስበስ የተናገሩት ሕወሀት ነፃ ሲያደርጉ  ይታያሉ። 

ካለፈው ዝግጅታን ቅዳሜ የካቲት 9 2011

From Los Angeles hager wodad archive (Feb 16,2019)

አገሬን ከሩቅ ሳያት

የኢትዮጵያ 6ኛው አገራዊ ምርጫ በሰኔ 14 ሰኞ ሊካሄድ ሕዝቡ እሁድ እኩለ ሌሊት ላይ በመሰለፍ የምርጫ ሰዓት መድረስን ሲጠባበቅ  ማየቱ፣  ቀኑን ሙሉ ረጅም ሰልፍ ላይ ቆሞ በፀሐይና በዝናብ ደከመኝ ሳይል በትእግስት ተራውን ጠብቆ አንዳንዱ ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ቆይቶ በመምረጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነቱን፣ ትዕግስቱንና ለዴሞክራሲ ያለውን ጥማት በተግባር አሳይቷል። ዐይን ላለው ለሚያይ፣ ጆሮ ላለው ለሚሰማ የምርጫው ሂደት በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው። 

 ይኼ የሰኞ ሰኔ 14 ቀን የምርጫ ሂደት በጣም ብዙ ነገሮች የታዩበት ምርጫ ነው። በመጀመሪያ የምርጫ ቦርዱ ከመንግሥት ገለልተኛ መሆኑ የታየበት፤  ምርጫውን ማስተባበሩ በአገር ደረጃ ምን ያህል ከባድና ፈታኝ እንደሆነ ያሳየበት፤ አገሪቱ ባለችበት የፀጥታ ሁኔታ ይኸንን ምርጫ ማከናወኑ፤የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የዳበረና ባለሙያ (professional) ተቋም መሆኑ የታየበት ጊዜ ነው። ምርጫ ቦርዱ እንደተቋም ከነጉድለቱ ጥሩ ሥራ በመሰራቱ መመስገን ይገባዋል፡ ሰህተቶችይታረማሉ። 

እዚህ ላይ አንድ ነገር መጥቀሱ ተገቢ ነው፤  ከምርጫው በፊት ከዋሽንግተን አመሪካ እስከ አዲስ አበባ ድረስ የተለያዩ ሚዲያ ነን ባዮች ምርጫ ቦርዱን በመጥፎ ገፅታ ለማሳየትና ተቀባይነት እንዳይኖረው ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልዋሹት ውሸት የለም። ምርጫ ቦርድ  በምርጫ ቀን አዋረዳቸው።   በምርጫው ቀን በቀጥታ የተለያዩ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች የሚስተላልፉትን  ሥርጭት በምስልም ሆነ  በቃል የሚታይና  የሚሰማ ተዘናግተን እናሞኛችሁ በማለት ኢትዮጵያውያ ውስጥ የሚነውን እያቀረቡ ከሚታየውና ከሚስማው ተቃራኒ ኢትዮጵያውያንና ምርጫ ቦርድን ለማሳነስ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ።   ፈረንጆች  ይኼንን ድርጊት pathetic  ይሉታል። 

◦ በሴ 14 ቀን ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነትና ትዕግስተኛነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሚዲያ ነፃ መሆኑን በአደባባይ በደንብ ያስመሰከረበት ቀነ። 

◦ የተለያዩ ጋዜጠኞች ትልቁን ትንሹን መራጭ ሲጠይቁ፣ ግለሰቦች መልስ ሲሰጡ ማየት በጣም ደስ ይላል፣ የመንግሥትና የግል ሚዲያ እኩል ሲሳተፉ ማየቱ ደግሞ የበለጠ ያረካል።

◦ ሌላኛው በሰኔ 14 የታየው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጨዋነት (maturity) ነው።   ሁሉም ፓርቲዎች ያሳዩት ሃላፊነት በጣም የሚደነቅ ነበር።   ምርጫው በሰላም እዲጠናቀቅ ክፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል። 

◦ የኢትዮጵያ መንግሥትም ፀጥታን በማስከበር ምርጫው በሰላም እዲከናወን ሀላፍነቱን ተወጥቷል 

◦ ኢትዮጵያውያ ላይ የተጋረጠው የውጭ አገራት፣  የዓለም አቀፍ ድርጅቶችና እገር ውስጥ ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ማለትም ምርጫው እንዳይካሄድ ከሚፈልጉት ጋረ በመናበብና በመተባበር የሰኔ 14 ቀን ምርጫ እዲከሽፍከፍተኛ ዘመጃ መካሄዱ የማይረሳ ነው።  ሆኖም ኢትዮጵያውያ አሸንፋለች።  ምርጫውን አጠናቀናል፣ የግድባችንም ውሀ ሙለት ይካሄዳል፣ ሱዳንም ከመሬታችን ለቃ ትወጣለች። 

ኢትዮጵያውያ በልጆቿዋ ሃይል  ትከበራለች!! 

ሀገር ወዳድ::